ምንጮቻችን ከከተማው እንደገለፁት፣ በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን ጋይንት
ወረዳ ንፋስ መውጫ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች፣ ለተቸገሩና በደርቅ ለተጎዱ
ወገኖች ለማገዝ ተብሎ ከለጋሽ ደርጅትና አገሮች የመጣ የእርዳታ እህል፣ የወረዳዋ አስተዳዳሪዎች ወዳጅና ጥላትን ሲፈጠሩ ከታዘቡ
ወገኖች አንዱ ደምበላሽ ይደግ የተባለ ግለሰብ በመጋቢት
6/2008 ዓ/ም እርዳታ ለመቀበል በተሰበሰበ ህዝብ ፊት፣ ለወረዳዋ የህዝብ ግንኝነት ሃላፊ በላቸው አላምረው የተባለ ካደሬን በዱላ
ጭንቅላቱን በመመታት እንዳወደቀው ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ ለማውቅ ተችሏል።
በመጨረሻም የእዚህ ወረዳ ሃላፊ ቤት ፅፈት የሆነ አቶ አያሌው ሽመቴ የተባለ
ካድሬ እረዳታ ለመቀበል የተሰበሰበውን ህዝብ በየቤታችሁ ሂዱ፣ እንደገና
ማን ደሃ ማን ሃብታም ብለን በመለየት እናጣራለን እንዳላቸው መረጃው ጨምሮ አስገንዝቧል።
No comments:
Post a Comment