የአማራ
ክልል ህዝቦች የሆኑ ዜጎች በአድስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ያለምንም መጠሊያ ተበትነው እንደሚገኙ
የገለፀው መረጃው፣ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች አስተያየታቸው ሲሰጡም፣ በኢሕአዴግ የሥልጣን ዘመን በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ
እየደረሰባቸው ያለው ሰቆቋ ከፍተኛ ሆኖ፣ በአማራው ህዝብ ላይም ከሌሎች ክልሎች በማይተናነሰ መልኩ የተለያዩ ሰቆቃዎችና
እንግልት እየተፈጸሙባቸው መሆኑን የገለፁት፣ በአዲስ አበባ ላይ
ያለመጠሊያ በረንዳ ላይ የሚገኙ ዜጎች፣ የአማራው ህዝብ እንደ ሌሎች
ክልሎች ሰርቶ ያፈራውን ለቆ እንዲወጣ ሲደረግ ሲገደል ንብረቱ እየተቃጠለ፣ ከበደኖ እና ከአርባ ጉጉ ጭፍጨፋ ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜው ደረስ
ሕይወቱን እያጣ በሃገሩ ላይ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ሲቆጠር ከቆየ ውሎ አድሯል ሲሉ ተናገሯል።
በዚህ መሰረትም ከአማራ ክልል ከተለያዩ ቦታዎች ማለትም ከጎጃም፣
ከጎንደር እና ከወሎ የመጡ የአማራ ተወላጆች ቀያቸውን በስርዓቱ በሚደርስባቸው ከፍተኛ በደል በመልቀቅ ወደ አዲስ አበባ ከተሰደዱ
ወገኖች ውስጥ፣ በተለይ ደግሞ እናቶች እና ህፃናት አደባባይ ላይ ካለምንም መኖሪያና መጠለያ ተጥለው በተለያዩ በሽታዎች
እየተሳቃዩ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።
No comments:
Post a Comment