በምስራቃዊ
ትግራይ ዋና አስተዳዳሪ የሆነች ያለም ፀጋይ የተመራ ግምገማዊ ስብሰባ በመጋቢት 13 /2008 ዓ.ም እንደተካሄደ የገለፀው መረጃው፣
የስብሰባዉ እጀንዳ ደግሞ ክራይ ሰብሳበነት ለማድረቅ፤ መልካም አስተዳደር ለማስፈና የከተማና የገጠር አስተዳዳሪዎች ለመፈተሽ የሚል
የነበረ ሲሆን፣ ተሳታፊዎች በአስተዳዳሪዎች ላይ ስም እየጠቀሱ በማስረጃ የተደገፈ ጠንካራ ገምጋም ከቀረበ በኋላ፣ የኔ ችግር ነው
ብሎ የሚቀበል ሰው ይቅርና አስተዳዳሪዎቹ ተገልብጠው ግምገማ ላቀረቡ ግለ ሰዎች አስፈሪ ቃላቶችን በመወርወር መልስ እየሰጡ እንደነበሩ
ለተሳታፊዎች መሰረት በማድረግ የደረሰን መረጃ አስረድተዋል።
በስብሰባው
ጠንካራ ግምገማ ከቀረበባቸው የስርአቱ ሽመኞች የአደግራት ከተማ ከንቲባ ተስፋልደት ሆኖ በተሳታፊዎች የቀረበበት በማስረጃ የተደገፈ
ሂስ የተወላገደ መልስ በመስጠት ለማለፍ ቢመኩርም፣ በመጨረሻ ግን ከስልጣኑ ወርዶ ጉዳዩ በሕግ መጣራት እንዳለበት እንደትገመገመ
ለማወቅ ተችለዋል።
እንደሚታወቅ
የተጠቀሰው የአደግራት ከተማ ከንቲባ በፈፀመው ተደጋጋሚ አስተዳደራዊ ጥፋቶችና ክራይ ሰብሳበንት በለፈው አመት በከተማዋ ነዋሪዎች
ተገምግሞ ከኋላፍነቱ መባረር እንዳለበት የተወሰነበት ሲሆን፣ የህዝብ ስሜትና አስተያየት ለመቀበል ፍቃደኛ ያልሆኑ የትግራይ ባለስልጣናት
ግን ምንም እርምጃ ሳይወስዱለት እስከ አሁን ድረስ በኋላፍነቱ እንዲቀጥል አድርገዉታል።
No comments:
Post a Comment