Monday, April 25, 2016

በትህዴን ድርጅት ህዝባዊ እንቅስቃሴ ምክንያት ጭንቀት ውስጥ የወደቁት የህወሓት/ ኢህአዴግ መሪዎች፣ ድርጅቱ ፈርሶ ስለተበተነ ወላጆችን ልጆቻችሁን ከትህዴን አምጧቸው በማለት የተጋጨና የተደነጋገረ ቅስቀሳ እያካሄደ መሆኑ ተገለፀ።



 ለህልውናቸው ብቻ ሲሉ ውጥረት ውስጥ የወደቁት የህወሓት /ኢህአዴግ ባለስልጣናት፣ በመነሳሳት ላይ ባሉት ወቅታዊና አዋጣሪ የህዝብ ጥያቄዎች ሻቅሎት ውስጥ በመግባት ወደመጨረሻው የሞት አፋፍ ወርደው ባሉበት፣ የትግራይን ህዝብ በየቀኑ በመሰብሰብ ስለ ትህዴን የትግል ድርጅት እያነሱ ለማጥላላት ላይና ታች የሚሉ ሆነው፣ በተለይ ደግሞ የትህዴን ድርጅት ስለ ፈረሰ እያካሄደው የነበረው ትግል አብቅቷል እያሉ፣ በሌላ ምላሳቸው ደግሞ ወላጆችን ከትህዴን ጋር ለሚታገሉ ልጆቻችሁን ከገባችሁበት ገብታችሁ አምጧቸው ካልሆነ እናንተን የምንታገስበት ጊዜ አብቅቷል በማለት እያስፈራሯቸው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
   በዚህ ጉዳይ ላይ ከላዕላይ አድያቦ ወረዳ በርከት ያሉ አባወራዎች የትህዴን ደጋፊዎችና አነሳሾች ተብለው፣ እስከ ክልል ድረስ ተወስደው ታጣቂ ሚሊሻ የነበሩትን የታጠቁትን መሳሪያ ተገፈው ባዶ እጃቸውን የተባረሩ ሲሆን፥ ለሲቪሎች ደግሞ ከባድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥተው በቅርብ ቀን ወደየቀያቸው እንደተመለሱ ተገልጿል።

No comments:

Post a Comment