Monday, April 25, 2016

ገዥው ስርዓት ኢህአዴግ እየተከተለው ያለው አሰራርና የስራ ሂደት ወጣቶችን ስራ ፈት በማድረግ ለስደት ተጋላጭ የሚያደርግ እንደሆነ ተገለፀ።



በመረጃ ምንጮቻችን መሠረት፣ ወጣቱ በራሱ ጥረት እራሱን የሚያስተዳድርበት ሙያ በሚጨብጥበት ጊዜ እንኳን፣ ሙያውን አጠናክሮ  በመቀጠል የገቢ ምንጩ ሆና እንድትቀጥል በመንግስት አካላት የሚደረግለት ማበረታቻ ለይምሰል የሚነገር ካልሆነ በስተቀር፣ ፍፁም በተግባር እንደሌለና፣ እንዲያውም የያዘውን ሞያ ትቶ እራሳቸው በነደፉት የጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ የሚፈፀም በገዥው ስርዓት ኢህአዴግ ፖለቲካ የተጨማለቀ አደረጃጀት እንዲሰማራ በማድረግ፣ በማይወጣው እዳ በመክተት በቁጥጥራቸው ስር ደንገርገር እያለ ዘላለም እስረኛቸው ሆኖ እንዲኖር ትልቅ ጥረትና እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን መረጃው አስገንዝቧል።
     በገዥው ስርዓት ብልሹ አሰራር የተማረሩት ወጣቶች ደግሞ የሚወዱትን ስራቸውንና አገራቸውን በመተው ስደትን የመጨረሻ አማራጭ አድርገው እየወሰዱት መሆኑን ከገለፀ በኋላ፣ ይህ አፋኝና ግፈኛ ስርዓት ተወግዶ ህዝባዊ መንግስት እንዲቋቋም የሁሉም ዜጋ ወቅታዊ ፍላጎት ሆኖ እንደሚገኝ ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

No comments:

Post a Comment