Friday, April 22, 2016

የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የሚያግዝ በሳይንሳዊ ምርምር የተደገፈ ዘመናዊ መሳሪያ በእርሻ ይሁን በሌላ ዘርፎች ካልገባ በስተቀር አሁን ባለው ሁኔታ ከፍ ሊል እንደማይችል ተገለፀ።



     በየጊዜው ቁጥሩ እየጨመረ በመሄድ ላይ ያለውን የኢትዮጵያን ህዝብ ለመመገብ በእርሻው ዘርፍ ቅድሚያ ተሰጥቶ መስራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው ያለው መረጃው፣ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ ኢኮኖሚን ለማሳደግ የሚያግዝ በሳይንሳዊ ምርምር የተደገፈ ዘመናዊ መሳሪያ በእርሻም ይሁን በሌላ ዘርፎች ለማስገባት እስካሁን መሰረታዊ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ ሊሰራበት ባለመቻሉ፣ ሁሉንም ህብረተሰብ ማዕከል በማድረግ ሲለካ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከነበረበት ተጨባጭ ለውጥ ሊያመጣ እንዳልቻለ ተገልጿል።
     የገዥው ስርዓት የኢህአዴግ አመራሮች በየጊዜው በእርሻው ዘርፍ በአጠቃላይ ደግሞ የአገርን ኢኮኖሚ በማሳደግ መጠነ ሰፊ ዘመቻ በማካሄድ፣ ፈጣን ዕድገት በማስመዝገብ ከአፍሪካ አብነት ሆነናል ያሉት፣ ነፍስ ወከፍ ዜጋን ያላካተተ ድምር ስሌት በመቀመር ያስቀመጡት አለምአቀፍ የኢኮኖሚን መስፈርት ያላሟላ በመሆኑ ፍፁም ተቀባይነት የለውም ሲል በባለሙያ ተደግፎ የወጣው መረጃ አስታውቋል።

No comments:

Post a Comment