በሶማሌ ክልል በሞያሌ ከተማና አካባቢዋ ባለፈው ሳምንት ከቅዳሜ ምሽት
እስከ እሁድ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በመጣው ኃይለኛ ጎርፍ፣ በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰ የገለፀው መረጃው፣
ያጋጠመው አደጋ ጉዳት እንዳያደርስ ለመከላከል በገዥው ስርዓት የተሰጠ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ይሁን በአደጋው ጊዜ የተደረገ አስቸኳይ
ረድኤት ባለመኖሩ ሦስት ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ በርካታ ቤቶችና ንብረት ደግሞ እንደወደመ ለማወቅ ተችሏል።
በመረጃው መሰረት የገዥው ስርዓት አስተዳደሮች ይህ ሁሉ ንብረትና ህይወት
እየወደመ ልክ ምንም አቅም ከሌለው ሰው ጋር በማዶ ቆመው ሲመለከቱ ማየት አሳዛኝ ሆኖ፣ የቀይ መስቀል ሰራተኞች ግን ባላቸው አቅም
ለማገዝ ላይና ታች ሲሉ የተጎዱትን በአምቡላንስ ወደ ጤና ተቋማት ሲያጓጉዙ የታዘቡ መኖሪያ ቤታቸው ወድሞ ከብቶቻቸውና ንብረታቸው
የተወሰደባቸው በእርባታ የሚተዳደሩ ሰዎች ደግሞ፣ መንግስት ከዚህ በላይ በምን ሊረዳን ነው? እያሉ እያማርሩ እንደነበር ለማውቅ
ተችሏል።
No comments:
Post a Comment