በመረጃው መሰረት፣ በዓደግራት በሁሉም የከተማው ቦታዎች ከአሁን በፊት የመጠጥ
ንፁህ ውሃ ለሁሉም ህዝብ ሊዳረስ አልቻለም በማለት በምትኩ በከተማ በሚገኘው ማከፋፈያ የተባለ ቦታ ማደል ተጀምሮ እያለ ብዙ ሳይቆይ
እንደተቋረጠ ከገለፁ በኋላ፣ ከተቋረጠበት ውቅት አንስቶ እስከ አሁን ነዋሪ ህዝብ ንፁህ ውሃ ኣጥቶ ለከፋ የማሕበራዊ ኑሮ በመጋለጡ
ህዝቡ መሬቱን ጠዋትና ምሽት ለሚመለከተው አካል አቅረቦ አውንታዊ መልስ ሊያገኝ እንዳልቻለ ለማውቅ ተችሏል።
በሌላ
ወገን ደግሞ በዚሁ ከተማ መፍትሔ ያጣ የመብራት መቖራረጥና መጥፋት በተፈጠረ ችግር፣ የሌላው ህብረተሰብን ችግር በመተው፣ በማሽነሪ የሚሰሩ ደርጅቶችና በንግድ በተሰማሩ አካላት እያስከተለው ያለው
ኪሳራ ከባድ በመሆኑ፣ ከግለሰብ አልፎ በአገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሰከተለውን ያለ ችግር ትልቅ መሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች መግለፃቸውን
ምንጮቻችን ከላኩልን መረጃ ለማውቅ ተችሏል።
No comments:
Post a Comment