Friday, April 22, 2016

በደቡብ ኢትዮጵያ ሻሸመኔ ከተማ እየተሰጠ ያለው ለቤት መሰሪያ የሚሆን መሬት፣ በባለሙያ ሳይጠና እየተሰጠ በመሆኑ መሬቱ እየተናደ የሰው ህይወት እየጠፋ እንዳለ ተገለፀ።



    በመረጃው መሰረት፣ በሻሸመኔ ከተማ የመኖሪያ ቤቶች ድርጅት መስሪያ ተብሎ ውስጣዊ ሁኔታው ሳይጠና የተሰጠው መሬት፣ ህዝቦች ቋሚ ቤት ሰርተው እንደገቡ መሬቱ ተደርምሶ የዜጎች ህይወት በከንቱ እየጠፋና ለበርካታ አመታት ለፍተው ያሰገነቡት ቤት እየከሰሩ ሰለሆኑ፣ ነዋሪዎቹ በአገኙት አጋጣሚ ምሬታቸው እየገልጡ መሆኑን ታወቀ።
   በዚህ ችልተኝነት የተሞላበትን የመሬት አስጣጥ ተከትሎ፣ በባለፈው አመት  በህጋዊነት ተሰጥቶ ለህዝብ አገልግሎት ለመስጠት በተሰራ  አዳራሽ  በማያዚያ 3/2008 ዓ/ም ሰኞ ቀን  በመፈረሱ በውስጡ ከነበሩት በርከት ያሉ ወገኖች፣ አሰር የሚሆኑ ሰዎች ወዳያውኑ ተቀብረው እንደሞቱና  ሌሎች ሰምንት የሚሆኑ ደግሞ  በከባድ ተጎዱተው እንዳሉ ከገለፁ በኋላ፣ በሰዎች ላይ እየደረሰ ያለው ሞትና ጉዳት የሚጠየቀው በሰልጣን ላይ የሚገኘው መንግሰት እንደሆነ የተለያዩ የህብረተሰብ አካላት በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።




No comments:

Post a Comment