Friday, April 22, 2016

“ጣና ፎረም” ስብሰባ ለአምስተኛ ጊዜ በባህር ዳር በተካሄደበት ህዝባዊ ዓመፅ እንዳይነሳ የሰጋው የኢህአዴግ ስርዓት፣ ከተማዋን በጥበቃ ወታሃደሮችና በደህንነት አባሎች ጥብቅ ቁጥጥር ስር አስገብቷት እንደሰነበተ ተገለፀ።




     በሁሉም ማዕዘን በመነሳት ላይ ባለው ህዝባዊ ተቃውሞ ስጋት ያደረባቸው የኢህአዴግ ባለስልጣናት፣ በባህር ዳር ከተማ ከሚያዝያ 8 እስከ 9 /2008ዓ.ም የተካሄደውን ጣና ፎረም ስብሰባ፣ ህዝቡ እንደ አንድ አጋጣሚ በመጠቀም በስርዓቱ አገዛዝ እየደረሰበት ያለውን አፈናና ረገጣ በስብሰባው ተሳታፊ የአገርና የተቋማት መሪዎች ፊት ጉዳቸው እንዳይጋለጥ ትልቅ ስጋት ስላደረባቸው፣ ይህንን ለመቆጣጠር የባህር ዳር ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ወታሃደሮችና የደህንነት አባሎችን በማሰማራት፣ ነዋሪውን ህዝብ የት ነበርህ? ወደየት ነህ? በሚሉ ጥያቄዎች ሲያስጨንቁት እንደሰነበቱ ለማወቅ ተችሏል።
    በተሽከርካሪዎችና በእግራቸው በየጎዳናው ሌትና ቀን ተገትረው ሲጠብቁ የሰነበቱት የስርዓቱ ተላላኪዎች፣ ህጋዊነት በሌለው መንገድ በሆቴሎችና በምግብ ቤቶች ሌሎች መጠጥ ቤቶች በመግባት እየፈተሹ ደስ ያላላቸውን ሰው ደግሞ በዱላ እየቀጠቀጡ ወደ እስር ቤት ሲያጉሩት እንደሰነበቱ መረጃው ጨምሮ ያስረዳል።                             


No comments:

Post a Comment