Wednesday, April 6, 2016

በኢህአዴግ ስርአት ሰላሙ ያጣ ሰላማዊ ትግል!!



በአንዲት አገር የሚኖር ሰላማዊ ትግል በአገሪትዋ የሚንቀሳቀሱ አገራዊና ብሄራዊ ፖለቲካዊ ድርጅቶች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውና ነፃነታቸው በሚገባ ተጠብቆላቸው በህዝቡ ውስጥ በሚያሰርፁት ሃሳቦች የሚመሰረት ብቻ ሳይሆን በመካከላቸው የሚኖር ልዩነት በማጥበብ እስከ ጥምረት ይሁን ውህደት ፍጥረው የያዙትን አላማ ግቡን ለማደረስ ምቹ ሁኔታ አላቸው።
በመሆኑም የያዙትን አማራጭ ፖሊሲና የፖለቲካ ርእየተ አለም ወደ ህዝቡ በማስተዋወቅ ጥቅሙንና ጉዳቱን ደግሞ በህዝቡ ንቃተ ህሊና እየተመዘነ ኡነታውን ለማወቅ የሚያስችለው ብቻ ሳይሆን። ህዝቡ በግልፅ በማደረግና ባለማደረግ የነቃ ስልት በመፍጠር ለገዢው ስር አት ደግሞ ሰፊ እድል እንዲፈጥርለት ተጽእኖ ይፈጥራል።
በመሰረታዊ ፖለቲካ ጽንሰ ሃሳብ ደግሞ ስልጣን ላይ ያለው ገዢው ፓርቲ በዋነኝነት የመንግስት ስልጣኑ በብቸንነት ቢቆጠጠረውም እንኳ ህዝቡ ከፍተኛ አምሳያ የሌለው አካል መሆኑን ለማድረግ የፖለቲካ ጥበብ እንቅስቃሴ የሚያስፈልገው መሆኑ ደግሞ ጥያቄ የሚያስነሳ አይደለም ።
ምክንያቱም ህዝብ የሃሳብ ልዩነት አማራጭ እንዲሁም የሚያሻውና የሚበጀው እንዲይዝና እንዲደግፍ በዋነኝነት ገዢው ፓርቲ ውይ ስርአት የህግ የበላይነት በሚያረጋግጠበት መልኩ ለሚንቀሳቀሱት ህጋዊያን የፖለቲካ ድርጅቶች በመጠንከር አስፈላጊውን እገዛ በማደረግ ማለት  ሰላማቸውን የሚያስተዋዉቁበት መደረኮች ማዘጋጀት፤ በሚዲያ አማራጭ ሃሳባቸው ወይ ፖሊሲያቸው እንዲሰራጭ ማደረግ፤ ፅህፈት ቤት ከፍተው ከህዝብ ጋር በነፃነት እንዲወያዩ ማደረግ፤ በቂ የሆነ የፋይናንስ እገዛ መበጀት፤ እያንዳዳቸው ከመበታተን ይልቅ ጥመረትና ውህደት እንዲፈጥሩ የማበረታታት ሃላፊነት አለው።
ይሁን እንጂ በአገራችን የህዝብ ስልጣን በማን አለብኝነት በሃይል እየቀማ  ያለው ገዢው ስርአት ባህሪና ተግባር ስንፈትሸው ደግሞ የተለየ ይሆናል።
ምክንያቱም ኢህአኤግ ወደ ስልጣን ከተቆናጠጠበት ጊዜ እስከ አሁን ድረስ የሚያደናግራቸው ስልቶች አንዱ ሰላማዊ ትግል አማራጭ እንደሌለው በመግለፅ ለዚህ ደግሞ በአብዛኛው ፓርቲዎች አገራችን  አቅፋቸው ያለች የብሄር ብሄረሰቦች የሚዛመድ ቁጥር የያዙ ተቋዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲፈጠሩ ማደረግ ሆኖ ህልውናቸው በሚመለከት ደግሞ ከማበር ይልቅ እንዲበታተኑ፤ ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙ የተለያዩ ደባዎች በመፍጠር ዱካቸው የሚከተል የስለያ መዋቅር ዘርግቶ እንዲሰናከሉ በማደረግ ላይ ይውላል። ሕገ- መንግስታዊ መብታችን ይከበር ብለው ህጋዊ ሰላማዊ ሰልፍ ለሚጠይቁ ወገኖች እገዳ ማደረግ፤ ሰልፉ ቢያካሂዱም ለሞትና ለእስራት እየተዳረጉ ሲሆኑ  እንዲሁም አንጋፋ ፅሃፊዎችና ፖለቲከኞች የስርአቱን ስለሚነቅፉና ሰለሚፅፉ ባልዋሉበት የሃሰት ውንጀላ ከፀረ ሰላም ሃይሎች ግንኝነት አላችሁ እየተባሉ በቁጥጥር ሰር ገብተው እየተሰቃዩ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው።
ታቋዋሚ ፓርቲዎች መብዛት የፓርቲ ጥንካሬ መገለጫ አይደለም፣ ይባስኑ ለአስተዳደሩ የሚያስቸግር የፖለቲካ ድርጅቶች በመሰብሰብ ምንጫቸው ማድረቅ ያለመረጋጋትና አንድነት እንዲያጡ እየተደረገ እንዳለ በአገሪቱ ውስጥ ተከስቶ ያለውን አደጋ ምስክር የማያስፈልገው ሃቅ ነው ።
በዚህ መሰረት በያዝነው ሳምንት የገዚው ጉጅሌ ጠቅላይ ምኒስተር ከተለያዩ የአገራችን ሙሁራን ባካሄዱት የይስሙላ መደረክ ተጠይቀው ሲመልሱ- ተቃዋሚውች በፓርላማ ወንበር ቢይዙ ባይዙ የሚያመጣው ለውጥ የለም ዋናው ጉዳይ የቡዙሃኑ ሃሳብና አስተያየቶች መቀበልና ማስተናገድ ከዚህ ባለፈ ደግሞ ሰፋ ያለ የፖሊሲ ክርክሮች የሚካሄድባቸው መድረኮች እንፈጥራለን ሲል በሌላ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ የፓርቲ ቡዙሃንነት መኖር ማለት የህልውና ጉዳይ ነው ሲል ተሰምተዋል።
ይህ ደግሞ  በየ ቀኑ የሚጠፋ ያለው የሰው ህይወት፤እስራት፤ ደብዛው እየጠፋ ያለው ወገን መሳለቅያ ከመሆን ባለፈ ሌላ የሚሰጠው ትርጉም የለውም፣ ይህ ስርአት እስካለ ድረስ ሰላማዊ ትግልና የሃሳብ ነፃነት ማበብና ለውጥ እንዲመጣ መጠበቁ የኢሀዴግ ባህሪ የሚፈቅድ አይደለም።  

No comments:

Post a Comment