Monday, April 18, 2016

በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በደረሰ ቃጠሎ የተማሪዎች ምኝታ ክፍሎችና ንብረት ወደመ – የየክልሉ ተማሪዎችም ወደ መጡበት እየሄዱ ነው።



የአካባቢው ነዋሪም ሆነ መንግስት በቶሎ ሊቆጣጠረው ያልቻለው ይኸው እሳት ቃጠሎ በዚህ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሄዱ የመጀመርያ አመት ተማሪዎች የመኝታ ህንፃና በርክታ ንብረቶች መውደማቸው ታውቋል።
 የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሰጡት አስተያየት ከሆነ ይህ የእሳት ቃጠሎ ለረዥም ሰዓታት የቆየ ሲሆን፣ መንግስት በአፋጣኝ ሊያጠፋው ያልቻለው አንድ ተንኮል ቢኖረው ነው፥ በተለይ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያና በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እየተነሱ ያሉ የሕዝብ አመጾችን ከሽብርተኝነት ጋር ለማያያዝና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህን ማሳየት የሚፈልገው የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ሆን ብሎ እንዲህ ያለውን ጥፋት አይፈጽምም ማለት አይቻልም ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ገለፁ።
 በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ መኝታቸው እና ንብረቶቻቸውን ያጡ ተማሪዎች በችግር ላይ እንደሆኑ የሚናገሩት  አስተያየት ሰጪዎች፣ ከክፍለ ሃገር የመጡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመጣል ወደ ቤተሰቦቻቸው ጋር መሄድ መጀመራቸውንም ዘግበዋል።






No comments:

Post a Comment