Saturday, April 2, 2016

በሰሜን እዝ የሚገኙ የሰረአቱ ወታደሮች የህዝቦች ገንዘብ በመዝረፍ ላይ መሰማራታቸው ታወቀ።



  ምንጮቻችን ከቦታው የላኩልን መረጃ እንዳመለከቱት፣ በሰሜን እዝ የሚገኙ የሰረአቱ ወታደሮች የህዝብ ገንዘብ በመዝረፍ የተሰማሩ በመሆናቸው፣  በውቅሮ ከተማ ውስጥ በመጋቢት 5/ 2008 ዓ/ም ወታደር መንግሰቱና አስር አለቃ ዘይኑ ይማም የተባሉት ከአንድ ሴተኛ አዳሪ ቤት ሲጠጡ አምሽተው ከለሊቱ 5 ሰአት አካባቢ በጉልበታቸው በመጠቀም ያላትን 700 ብር ዘርፈው ሲውጡ ባሰማችው ጩህት በጎረቤት ሰዎች ትብብር እንደተያዙ ለማውቅ ተችሏል።
 
  መረጃው ጨምሮም፣ እነዚህ የሰረአቱ ወታደሮች በህዝብ ላይ እያደረሱት ያለው በደልና ወንጀል አሁን የተጀመረ ሳይሆን፣ ለበርካታ አመታት የቆየና እየተባባሰ የመጣ መሆኑን የአካባቢው ህዝብ ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኝ ታውቀ።



No comments:

Post a Comment