ከወጣቶቹ መካከል የተወሠኑትን ለመጥቀስ፦
-ሮቤል ተወልደ ከምስራቅ ዞን ጋንታ አፈሹም
ወረዳ ብዘት ከተማ
-ተስፋዓለም ወልደ ገብርኤል ከምስራቅ ዞን
ጉለማካዳ ወረዳ አዲስ ተስፋ ቀበሌ -ገብረ ፃድቅ ኤልያስ ከማዕከላዊ ዞን ላዕላይ ማይጨው ወረዳ ሳግላሜን ቀበሌ
-ሃየሎም ወሉ ከማዕከላዊ ዞን ናዴር አዴት
ወረዳ ዳግነ ቀበሌ
-ገብረ ስላሴ ጉዕሽ ከማዕከላዊ ዞን ናዴር
አዴት ወረዳ ዓዲ ሶራዋት ቀበሌ
-ኃይሌ አለማየሁ ከሰሜን ምዕራብ ዞን ላዕላይ
አድያቦ ወረዳ ዓዲ በጊዕ ቀበሌ
-ደጀን ፀጋይ ፤ተክሊት መኮነን ፤ዓውደ ሰላም
አማን እና አማኑኤል ጌታቸው ሁሉም ከሰሜን ምዕራብ ዞን ታህታይ አድያቦ ወረዳ ባድመ ቀበሌ
-መንግስት አብ ሃጎስ ከሰሜን ምዕራብ ዞን
ታህታይ አድያቦ ወረዳ ጎማሃሎ ቀበሌ
-ተስፋይ ጥላሁን ከሰሜን ምዕራብ ዞን ታህታይ
አድያቦ ወረዳ ዓዲ አውዓላ ቀበሌ፥ የሚገኙባቸው ሲሆን፣ በትጥቅ ትግል እንዲታገሉ ካስገደዳቸው ምክንያት ሲጠቅሱ የተዛባ የፍትህ
አሰራርና በስራ አጥነት ምክንያት ለከፋ ድህነት ተጋልጠው በከፍተኛ ችግር ተዘፍቀው በመቆየታቸው ተማረው ወደ ትጥቅ ትግል ለመግባት
እንደወሰኑ ገልፀዋል።
በተለይም ወጣት ደጀን ፀጋይና ዓውደ ሰላም አማን እንደገለፁት፣ በስልጣን
ላይ ያለው ስርዓት እየተገበረውና እየተከተለው ያለው የትምህርት ፖሊሲ ትውልድን የሚገነባ ሳይሆን፣ ትውልድን ለኋላቀርነት የሚዳርግ
በመሆኑ አምራች ኃይሉ ወጣት ትምህርት ጨርሶ አቅሙን ሊያጎለብት ባለመቻሉ፣
ስራ ፈት በማድረግ ወደ ድህነት የሚያዘቅት እና የእለት ጉርስን ለማግኘት ስትል ተገደህ ወደ ውትድርና እንድትቀጠር የሚያደርግ መሆኑን አስረድተዋል።
No comments:
Post a Comment