Monday, April 25, 2016

በኢትዮጵያ አጋጥሞ ያለው ከባድ ደርቅ እያስከተለው ያለው ረሃብ የተረጅው ቁጥር ከጊዚ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሂድ የዜጎች ሞት እንዳያሰከትል አለም አቀፍ የሰበአዊ ደህንነት ያላቸውን ስጋት ገለፁ።



መስሪያ ቤቱ  እንደገለፀው፣ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው እርዳታ የሚጠቁ ዜጎች 20 ሚሊዮን ደርሶ እንዳለ የገለፁ ሲሆን፣   በተለይ ደግሞ በድርቁ የተነሳ  በረሃብ የተጠቁ አካባቢዎች ከ186 ወደ 219 ከፍ እንዳሉ ከገለፀ በኋላ፣ እርዳታ ጠባቂ የሆኑ ዜጎች ደግሞ በጊዜው በቂ የሆነ እርዳታ ሊያገኙ ባለመቻላቸው፣ ወደ ከፋ ረሃብ በመግባታቸው ምክንያት በአንዳንድ አካባቢዎች ቀያቸውን ለቀው ወደ ስደት  መሔድ እንደ ጀመሩና፣   በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ አደጋው ወደ ሞት እያመራ እንደሆነ አስጠነቀቀ።
   በተጨማሪም የተባበሩት ህብረት ደርጅት አገሮች ከአለም አቀፍ  የጤና ደርጅት ጋር በመሆን፣ በድርቅ ጤናቸው ለተጎዱ ኢትዮጵያዊያን እንዲውል የተባለ በሚሊዮን ዶላር የሚገመት ውጭት የተደረገበት በጁቡቴ ወደብ የገባ እርዳታ፣ በኢትዮጵያ መንግሰት በኩል የተሰተካከለ ፈጣን አገልግሎት መጓጓዣ ባለመኖሩ፣ በወደብ ተከማችቶ ቀኖች እየቆጠረ በአስቸኳይ  በድርቁ ለተጎዱና እርዳታ ለሚጠብቁ ህዝቦች በአጭር ወቅት ከልታገዙ ደግሞ ለከባድ የሞት አደጋ እያመሩ መሆኑን የሚያሳሰብ ጉዳይ እንደሆነ በተለያዩ ሪፖርቶቻቸው  በማጋለጥ ላይ ይገኛሉ።

No comments:

Post a Comment