Monday, April 11, 2016

በሙስና ዉስጥ ተዘፍቀህ ሙሱናን መጥፋት አይቻልም!



     እንደሚታወቅ በአንዲት አገር በፀረ ሙስና ኮሚሽን የሚካሄድ ትግል ግቡን የሚመታ ለሙስና የሚያስወግድ በጥናትና ጥብቅ ክትትል የተመሰረተ ህጋዊና አስተማሪ እርምጃ ሲወሰድ እንጂ፣ በሙስና የተዘፈቁና እጃቸው ጨምረው እንደፈለጉት በሚያድርጉት የመንግስት አካላት ለይስሙላ ነጋ ጠባ ሙስናን ከምንጩ ለማድረቅ እንታገል ብለው ስለ ደሰኮሩ ብቻ መፍትሔ ሊሆን አይችልም።
    ምክንያቱ ሙስናን ለማጥፋት በመጀመርያ ሙስናን ለመከላከል የቆመ አካል ንፁህና ታማኝ መሆን አለበት፣ እንዲሁም ለሚደረግ የፀረ ሙስና ትግል ከመፈከር ያለፈ እየተከታተለ በተግባር የተሰኘ ከስር መሰረቱ ለመጥፋት ቆራጥነት ካለ፣ የፀረ ሙስና ትግል ከጫፉ ሳይሆን በስር ላይ ነው ማተኮር ያለበት።
   ስለሆነም ለመንስኤው ከመስረቱ አጥፍተህ ለመጣል የሚቻል ደግሞ የአገራቸውንና ህዝባቸው ወዳጅ የሆኑት ዜጎች ለትግሉ በዋነኝነት እንዲያንቀሳቅሱት ቦታ ሲሰጣቸው ብቻ ነው።
 በመሆኑ ደግሞ ለሚደረግ የፀረ ሙስና ትግል  በተናጠል ሳይሆን ተደራጅቶ የተጠናከረ የህዝብ ጠንካራ ተሳትፎ ሲኖር ነው።
 የኢህአዴግ መሪዎች ለህዝብ እና ለአገር የሚቆረቆሩ በመምሰል በመደናገር ተግባሮች ተጠምደው ከሚገባቸው ዉጭ በጥቅም መተሳሰር ፈጥረው፣ ጥቂቶች እንዲጠቀሙ ብዙዎች ግን እንዲጎዱ ሲያድርጉ ቆይተዋል አሁንም እየቀጠሉበት ይገኛሉ።
 በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ ከሙስና የፀዱ የመንግስት ተቋማት የሆኑት ፅህፈት ቤቶች ፈልገህ ለማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው። ከዚህም አልፎ እስከ ትምህርት ቤቶች፤ የጤና ተቋማት፤ የሃይማኖት ቦታዎችና ሌሎች ሙስናን ስር ሰዶ ጭቁን ህዝባችን በየቀኑ ሲጎዳ ይታያል።
በተለይ ከፍተኛ በጀት የሚወጣላቸው የስርአቱ ትላልቅ ፕሮጀክቶች፤ ፅህፈት ቤትና ተቋማት ዉስጥ ሙስናን ከቁጥጥር ዉጭ ሆኖ ይገኛል።
የኢህአዴግ ባለስልጣናት ራሳቸዉን የሚዘርፉት የህዝብ ሃብት ነጋ ጠባ በሚድያዎቻቸው ይሁን በተለያዩ መድረኮች፣ ሙስናን የሚያድርሰው አደጋ ሲደሰኩሩና እንዲሁም ከፅህፈት ቤቱ ዋና ኦዲተር የሚወጡ ሪፖርቶች በተደጋጋሚ የሚታዩ ህግና ስርአት ያልተከተሉ ገበያዎችን፣ በሚገባ የሚያወራርድ ሂሳብ እንደሌላቸው እየተባለ የሚገለፁ እንኳ ቢሆኑ፣  በተግባር ግን የሚወሰድ ቆራጥ እርምጃ ባለመኖሩ ፍከራ ከመሆኑ ውጭ የሚታይ ለዉጥ የለም።
     ከኖረም በፖለቲካዊ እምነቱና አስተያየቱ የተፈለገ አካል በታርጌት ዉስጥ አስገብተህ መጨበጫ የሌላቸው ብዙ የሀሰት ክስ በማቅረብ በእስር ቤት እያሰገቡ በሙስና ተዘፍቆ አግኝተነዋል ይባል ይሆናል። እዉነቱ ግን በአንፃሩ ነው። ምክንያቱ ለሙስና ዋናዎቹ ራሳቸዉ የበላይ ባለስልጣኖችና መረበባቸዉን ስለ ሆኑ ነው።
ሙስና በስፋት የተስፋፋባቸው ድርጅቶች፣ ትላልቅ ተቋማትና ፅህፈት ቤቶች በደምብ አድርገው ያዉቃሉ። በዚህ ሙስና ዉስጥ እጃቸዉን አስገብተው በከፍተኛነት የሚያሽከረክሩት ይታወቃሉ ብቻ ሳይሆን፣ ህዝብ አንድ አንድ ጊዜ ባገኘበት የመድረክ ቀጥታዊ ተሳትፎና እድል  የሙስናን ጠንቅ ወደ ኋላ ሳይል በመጋለጥ ላይ እያለ፣ ሙስናን ለምንድ ነው ስር ሰዶ ከፍተኛ ቦታን ለመያዝ የቻለ? በአንድ በኩል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ፀረ ሙስና ኮሚሽን በዉስጡ በከፍተኛነት የሚመሩት አካላት ብሙስና ተጨማልቀው እያሉ ለምንድ ነው አስቀድመህ እነሱን እንዲባረሩ ወይም አስተማሪ እርምጃ ያልተወሰደላቸው? ሁሉም ለሀገር የሚቆረቆር ወገን ሊጠይቀው የሚገባ ጉዳይ ነው።
ምክንያቱ የሙስናን ጠንቅ ሆነው በሙስና ኪሳቸው ያሳበጡ ሃላፊዎችና መረበባቸው የዘረጉትን ችላ ተብለው እየታለፉ፣ ለዛ በነሱ ምክንያት ሲንከራተት እየዋለ ያለው ንፁህ ወገን በተለመደ የመደናገርያ ቃላት፣ በስርአቱ ሚድያዎች ተድበስብሶ እንዲታለፍና እንዲሁም በመላው የአገሪቱ አከባቢዎች፣ በሙስና ራቆቱ ያወጡት አካላት፣ ተመልስው ወደ ነበሩበት ቦታ እንዲይዙ እየተደረገ እያየና እየሰማ ላለው የህብረተሰብ ክፍል፣ ሙስናን እየተዋጋን ነው ብለህ መደስኮር ከመቀለድ አልፎ ሌላ የሚሰጠው ትርጉም የለውም። ስለዚህ በሙስና ዉስጥ ተዘፍቀህ ሙስናን መጥፋት አይቻልም።


No comments:

Post a Comment