Monday, April 18, 2016

የይስሙላ ልማታዊ መንግስት በኢትዮጵያ!



ህዝብንና አገርን ለመለወጥ የፈለገ ስርአት የአገሪቱ ሃብት ተጠቅሞ  የልማት  ፈጣን ተሳትፎ  በተሻሻለውን መንገድ እየመራ የዜጎች ነፃነትንና መብትን በመጠበቅ  የህብረተሰቡ ጥያቄና ፍላጎት ለሟሟላትና  ወደ ተግባር  እንዲውል በትጋት  የሚንቀሳቀስ  ስርአት ከሆነ ልማታዊ ሊባል ይችላል፣፣

  አንድ ስርአት ልማታዊ ባህሪ አለው ሊያሰኘው የሚችል ደግሞ፣ የጠራ ፖሊሲ ቀርፆ ከቢሮክራሲ አሰራርና መጉላላት የነጣና የተስተካከለ የአስተዳደር አስራር በመዘርጋት፣ በህዝብ ላይ ጥሩ አመኔታና ተቀባይነት አሳድሮ፣ ልማት የህልውና ጥያቄ ዋስትና አድርጎ በመወሰድ  የህዝብ የኑሮ ደርጃን ለመለወጥና  ለማሻሻል  በቅንነት ሲሰራ ብቻ  ነው፣፣
 
    የህዝብ አመኔታና ድጋፍ የሌለው በስልጣን ላይ የሚገኘው ገዥው የኢህአዴግ ስርአት ግን ይህን አስተሳሰብ አዳብሮ በመሬት ላይ ወርዶ የ ኢትዮጵያ ህዝብ ኑሮ የሚያሻሽል እድገት ያመጣል ተብሎ ሊጠበቅ አይችልም፣፣
     በዚህ ሳብያም   ልማታዊ መንግስት ነኝ እያለ  በመደስኮር  የሚገኝው አምባገነን ስርአት፣  በባህሪውና  በተግባሩ  ሲታይ የዜጎችን ነፃነትና መብት ረግጦ ግልፅነትና ተጠያቂነትን በሌለው  ቢሮክራስያዊ አስተዳደር  በመስፋፋት   በጥቅም ያሰባሰባቸው ቡዱን በመሰማራት የህዝብን አደራና እምነት ወደ ጎን በመተው  ግላዊ ጥቅም ለመካበት ልክ እንደ ምስጥ  የህዝብ ገንዘብ እየቦረበሩ እድገት እንዳይመጣ  እንቅፋት  በመፍጠር ላይ ስለ ሚገኙ፣ የህዝብ መብትና ጥቅም  ሊከበርለት ይቅርና ልማታዊ መንግስት በሚል ሽፋን በአዲሱ  በትር ሲጨፈጨፍት ይታያል፣፣

  የኢህአዴግ መሪዎች ከተወሰኑ አገሮች እየገለበጡ የሚነድፉት ስትራተጂካዊ ልማት ሁሉም ትክክል አይደሉም ባይባሉም አብዛኞዎቹ  ከአገራችን ተጨባጭ  ሁኔታ  የማይጣጣሙ በመሆናቸው  የሚያደርሱት ኪሳራ ከባድ ነው፣

    በዚህ ውጤት አልባ በሆነው ስትራተጂ ሽፋን ስም ተላብሶ ልማታዊ  ለመምሰል የውሽት ሪፖርት   በማቅረብ   በየጊዜው በጭቁኑ  ወገናችን  በግፍ ላይ ግፍ ከመፈፀም  በስተቀር ሌላ ውጤት አልተገኘለትም።
  ምክንያቱም ህዝባችን  አንዳችም ፍሬ ሳያገኝ በባዶ ተስፋ ምቾት  ሲጠብቅ እነሱ ግን ተጠያቂነት  በሌለበት የህዝብ ሃብትና ገንዘብ  እንደፍላጎታቸው   በመዝረፍ  በጥፋት ጎደና  እየተጓዙ  ልማትና ሰላም ከማምጣት ይልቅ   የግፍ በትር  በማንሳት ማን ያሸንፈናል እያሉ ጉራቸውን በመንዛት  እንደቆዩና አሁንም  እንዳሉ  በግልፅ እየታዬ ያለ ሃቅ በመሆኑ ጥያቄ የማያስፈልገው እውነታ ነው፣፣
  የኢህአዴግ መንግስት ልማታዊ ነኝ በሚል ሽፋን  ጥቅሙ  ለህዝብ ሳይሆን  ስልጣኑን ለማቆየት  ሲል ለቡዱኑ ጥቅም  አዋለው ብቻ ሳይሆን፣  ከልማታዊ መንግስት የማይስማማ  የቢሮክራሲ  አስተዳደር  በመገንባት ህዝብ ነፃነት እንዳያገኝ አግዶ በፁኑ ክትትልና ጥበቃ በማሰገባት  የስልጣኑ እድሜ ለማራዘም              በመደናበር  ላይ ይገኛል፣፣
   ኢህአዴግ  ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት ሰፊ ወይይትና ክርክር ኣካሂዶ እውንታዊና  አሉታዊ በመገምገም  ህዝብ ከደረሰበት ችግር የሚገላገልበት መሰረታዊ የሆነ መፍትሄ ለማምጣት ከተሳነው እንሆ የአንድ   ወጣት እድሜ አስቆጥረዋል፣፣
 በመሆኑም ህዝብ በአሁኑ  ጊዜ  ብሄራዊ አንድነቱን አጥቶ ስትራተጂካዊ ጥቅሞችና ፖለቲካዊ ተሳትፎውም በጥቂቶች እናውቅልሃለን በሚሉ  መሪዎች በመርገጡ ምክንያት ስር ነቀል ለወጥ ሊያመጣ ኣልቻለም፣ ምክንያቱም ለጥቂቶችና ለግብረ ኣበሮቹ  ወንበርና ስልጣን  ተብሎ የተሴረ  ልማታዊ መንግስት  በተግባር ሲታይ አደጋ እንጂ ለህዝብ  ሊፈይደው ኣልቻለም፣፣

   በዚህ ሳብያም ገዥው የኢህአዴግ ስርአት ቃሉና ተግባሩ  አይጣጣምም  ብቻ ሳይሆን፣ በስርአቱ አስተሳሰብና ፍላጎት ብቻ ህዝብን ወጥሮ በመያዝ  ከልማት ጎደና ወጥቶ እንዲቆም፣ እንደዚሁም የመንግስት አደረጃጀት ሙሉ በሙሉ ለፖለቲካ ፍላጎቱ  ስለአዋለው   ህዝባችን ነፃነት እንዳያገኝ  በእጅጉ ተቸግሮ ይገኛል፣   በህዝብ ስም  ያገኘው  ስልጣን  ቢሆንም  ለልማታዊ ስራዎች ማስፈፅምያ ከመዋል ፈንታ ለሩብ ዘመን ያህል የዘለቀው የብልሽውናና  የቢሮክራሲ ኣስራር  መርህ  መበጣጠስ ተስኖት፣ የስልጣን ህልዉናዉ  በገደል ኣፋፍ ሰለደረሰ  አሁን ለማስመሰል  ሲል ንፁህን ዜጎችን ነጋ ጠባ ስብስባ እያለ  ጠምድዋቸው ይገኛል፣፣
      በመሆኑም ልማት የህልውና ጥያቄ ሊሆን የሚችለው ህዝብ  መብቱና ነፃነቱ ተጠብቆለት  በቂና የተሰተካከለ አስተዳደር አግኝቶ  በልማታዊ ስራዎቹ በነፃ ሲንቀሳቀስ  ነው፣ ይህ ደግሞ ከኢህአዴግ  ሊገኝ እንደማይችል አውቀን ለህልዉናችን መነሳት ይገበናል፣፣         


No comments:

Post a Comment