Saturday, May 14, 2016

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የመልካም አስተዳደር ችግርና ኪራይ ሰብሳቢነት በከፍተኛ ሁኔታ እንደተስፋፋና ልቅ እንደሆነ ተገለፀ።



የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮች በአገሪቱ ካሉት የዩኒቨርስቲ ተቋማት ሁሉ የከፋ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው። ሰንበቴ የተባለው የዩኒቨርስቲው ፕሬዚደንት ከሌላ ቦታ ተቀይሮ ከመጣ በኋላ ዕለታዊ የሚፈጠሩ ችግሮችንና የሚቀርቡለትን አቤቱታዎች ህግና አሰራሩን ተከትሎ መልስ ከመስጠት ይልቅ በአንፃሩ በማስፈራራትና በግለሰቦች እየተቦደነ አቅጣጫው የጠፋበት አስተዳደራዊ ሙስና በማስፋፋቱ በግቢው ሰራተኞችና አጠቃላይ በዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ቁጣ አስነስቶ እንዳለ ታወቀ።
   በተለይ ይህንን ክፍተት ተጠቅመው በኪራይ ሰብሳቢነትና ሙስና ውስጥ ከመዘፈቃቸው በላይ በተቋሙ በኔትወርክ ወይም በአንድ ለአምስቱ መረብ አካባቢያዊና ዘረኝነት የተላበሰ አሰራር እንዲስፋፋ በር ከፍቷል ያለው መረጃው በዚህ የተነሳ ደግሞ መፍትሄ ያጡ የዩኒቨርስቲው ሰራተኞች ሞራላቸውና የስራ ወኔያቸው ቀንሶ ከተቋሙ ለቀው የሚሄዱት ሰራተኞች ከቀን ወደቀን እየጨመረ በመሄድ ላይ እንዳለ ታውቋል።
    በመጨረሻም በአሁኑ ወቅት በዩኒቨርስቲው ውስጥ ውጥረትና ያለመረጋጋት ተፈጥሮ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።


No comments:

Post a Comment