Friday, May 6, 2016

ለህዝብና ስለሃገር ታላቅ ዋጋ እየከፈሉ የሚገኙት ወገኖች በርከት ያሉ በመሆናቸው ስርዓት አመራሮች ከባድ ጫና እየደረሰባቸው እንዳለ ተገለፀ።



ባገኘነው መረጃ መሰረት ለህዝብ ሲሉ በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ በስርዓቱ ታስረው በየእስር ቤቱ የሚገኙ ወገኖች በርካታ እንደሆኑና  ከእነዚህ መካከል በአርባ ምንጭና በሰሜን ጎንደር የሚገኙ የአንድነት ፓርቲ አባላት የሆኑ ዜጎች አምስት ልጆቻቸውና ሚስቶቻቸው በወያኔ ኢህአዴግ የሚደርስባቸው ተፅዕኖ ስራ መስራት እንዳልቻሉና በችግር ላይ ወድቀው እንደሚገኙ በመግለፅ የመታሰሪያቸው ምክንያት ደግሞ ወንጀል ሰርተው ሳይሆን ስርዓቱ በፈጠረው አስተዳደራዊ ችግር በመቃወማቸው ምክንያት በመሆኑ በአሁኑ ጊዜ በቅሊንጦስ ማዕከላዊ እስር ቤትና ሌሎች እስር ቤቶች ታጉረው ለከባድ የማህበራዊ ኑሮ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ ታውቋል።
    እነዚህ ወገኖች የታሰሩበት ምክንያት ለሃገራችን ህዝቦች ሲሉ እየተካሄደ ያለውን ትግል በመደገፍ ዋጋ እየከፈሉ እንደሚገኙ በእስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ የሚገኙ ንፁሃን ዜጎች በጣም በርካታ እንኳን ቢሆኑ ከእነዚህ ውስጥ ተመስገን ደሳለኝ ፤አንዳርጋቸው ፅጌ ፤አብርሃ ደስታ፤አስቴር ስዩም ፤እንግዳው ዋኘው ፤በላቸው አወቀና ሉሉ መለሰ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ሲሆኑ በላያቸው ላይና በቤተሰቦቻቸው ላይ እየደረሰ ያለው በደል ደግሞ የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑን ተረድተን ስርዓቱን የማስወገድ ስራ አጠናክረን ልንሰራ ይገባል ሲል ህዝቡ በመግለፅ ላይ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ አስታውቋል።

No comments:

Post a Comment