Friday, May 6, 2016

የአሜሪካ መንግስት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ መፈታት እንዳለበት ለኢትዮጵያ መንግስት ጥሪ አቀረበ።



     የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ የአውራምባ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ እየሰራ በነበረበት ወቅት እኤአ ሰኔ 19ቀን 2011ዓ.ም በወያኔ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ታስሮ እስካሁን ድረስ በእስር ላይ የሚገኝ ሲሆን የአሜሪካ መንግስት ሚያዝያ 24 2008ዓ.ም ጋዜጠኛው መፈታት እንዳለበት ለኢትዮጵያ መንግስት ጥሪውን እንዳቀረበ ለማወቅ ተችሏል።
    ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ የታሰረበት ምክንያት ከመታሰሩ በፊት ለመንግስት የሚወቅስ ፅሑፍ ፅፈሃል በሚል ምክንያት እንደሆነ አንድ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ባወጣው ዝርዝር መረጃ እስታውቋል።
   በተመሳሳይ ዜና በዚህ ሰሞን የጋዜጠኞች መብት ተጣባቂ ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ከሶማሊያ ፤ከሳዑዲ አረቢያና ከሊቢያ ቀጥላ በአራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣ እንደምትገኝ ከገለፀ በኋላ ከአፍሪካ አገሮች ደግሞ ጋዜጠኞችንና ፀሐፊዎችን በማሰር በቀዳሚነት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተመድባ እንደምትግኝ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) ገልጿል።

No comments:

Post a Comment