Saturday, May 7, 2016

የከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች ተጠያቂ ባልሆኑበትና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር በተስፋፋበት ስርዓት ውስጥ መልካም አስተዳደርን ማስፈን እንደማይቻል ተገለፀ።




በከፍተኛ የፖለቲካ አመራሩ እርምጃ የሚወሰደው በሂስና ግለሂስ ስርዓት ብቻ በመሆኑና ይህ የመመዘኛ ስርዓት በራሱ ችግር ያለበት በመሆኑ በከፍተኛ የፖለቲካ አመራሩ ውስጥ ያለው ወገንተኝነትና ኪራይ ሰብሳቢነት ካልተፈታ መልካም አስተዳደር ማስፈን እንደማይቻል በመግለፅ ቤስት ስኮር ካርድ (ቢኤስ ሲ) የሚባለው መመዘኛ የሰራተኞችን የስልጣን አገባብ መመዘን ቢችልም እንኳ በከፍተኛ የፖለቲካ አመራሩ ላይ ሲደርስ ስለማይሰራ የፖለቲካ አመራሮች በህግ የሚጠየቁበት መመዘኛ እንደሌለ ተገልጿል።
    እስካሁን ድረስ ሰራተኞች በዘገምተኝነት በቸለልተኝነትና ለአመራሮች ባላቸው ታማኝነት ስለሚመዘኑ የውጤት አስጣጡ ቸለልተኝነት የሰፈነበት በመሆኑ አንዳንድ መመዘኛዎች በቅርበት በኔትወርክ በዝምድና ወይም በጓደኝነት እንዲሁም ለገዥው ፓርቲ አመራሮች ባላቸው ታማኝነት በመሆኑ ችግሩ በሁሉም ተቋማት ውስጥ ይነስም ይብዛም ተስፋፍቶ እንደሚገኝ ተግለጸ።                                         


No comments:

Post a Comment