Thursday, June 30, 2016

በአስመሳይ የሲቪል ሰርቫንት ቀን የሚመጣ ለዉጥ የለም!!



  የህዝብ ውክልና ሳያገኝ  በስልጣን  እየቀጠለ የሚገኘው  የህወሓት  ኢህአዴግ  ስርአትና መረቡ ከቅንነትና ከህዝባዊ ኣግልግሎት ወጥቶ ለግላዊ ጥቅሙ  ብቻ  መሰመራት ከጀመረ ሩብ ዘመን አስቆጥረዋል ብቻ ሳይሆን  ህዝባችን  የተታገለበትንና  ምርጥ ልጆቹን መስዋእት  እየከፈለ  ይመኘው የነበረው  ሰላም፤ ፍትሕ፤ ዴሞክራሲና መልካም ኣስተዳደር  ተክዶ  ፍላጎቱና ተስፋው መና ሆኖ ቀርቷል።
       ይህ በእንዲህ  እንዳለ  የህወሓት  ኢህአዴግ መሪዎች  ከህዝብና ከሃገር ሃብት የዘረፉትን ገንዘብና ንብረት ተጠቅመው  አይተዉት  የማያውቁትን ሃብትንና ንብረት  ሲያደልቡ  በተቃራኒው  ጠዋሪ ያጣ  የሰማእታት ቤተሰብና ከእጁ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ የሚመራው  አብዛኛው ድሃ ህብረተሰባችን   በተለያዩ ደረጃ ከሚገኙ ካድሬዎችንና አስተዳደሮች ተገቢ ፍትህና ቀና ግልጋሎት አጥቶ እየተመዘመዘ ሊወጣው ወደ ማይችልበት  ድህነት አጋልጠውት  ይገኛሉ።
   እውር ለእውር ተያይዘው ወደ ገደል እንደሚባለው  ሁሉም  በስልጣን ላይ የሚገኙ  የህወሃት ኢህአዴግ  መሪዎች  በሚልዮኖች የሚቆጠር  የህዝብና የሃገርን ሃብት ያለ ተጠያቂነት በመዝረፍ  ሰማይ  ጠቀስ ፎቆችን በመስራት  በስውርና በገሃድ ሲበለፅጉ ለዚህ ብልሹ   የሆነ ተግባራቸው ተከታትሎ ወደ ህግ ቀርበው እንዲጠየቁና   በህግ መስረት  እርምጃ የሚወስድ ኣካል ባለመኖሩ  ከህጋዊ አሰራር ወጥተው ወደ የጥፋት መንገድ  በመሰማራት  ይኸው 25 አመታት አስቆጥረዋል።
   በዚህ መሰረት የላይኞቹ መሪዎች አካሄድ  ተከትለው የታችኞቹ አስተዳደሮች ህዝብ አገልግሎት ሊያገኝ ወደ ተለያዩ ፅህፈት ቤት በሚሄዱበት ግዜ በቀነ ቀጦሮ እንዲመላለስ አድርገው ጉቦ እንዲሰጣቸው  በመገፋፋት  በሙስና ተግባር  ተሰማርተው   ህዝብን   የሚያጉላሉ  አካሎች ስፍር ቁጥር የላቸውም።
   የህወሃት ኢህአዴግ አመራሮች  ይህና ሌሎችም ፀረ ህዝብ  ተግባሮቻቸውን ስር ሰዶ ባለበት ግዜ  ሰኔ 16   የሲቪል ሰርቫንት ቀን እያሉ በየአመቱ  በማላገጥ  ሲለፈልፉ  በተቃራኒው ህዝባችን ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጦ  ባለበት ጊዜ  በተግባር የሌለ  አመት በመጣ ቁጥር ሲሙሉና  ሲደሰኩሩ እየታዩ ናቸው።
      ህወሃት ኢህአዴግ  በአሁኑ ሰአት  በመላ አገሪቱ  በመቀጣጠል ያለውን ጭቆና የወለደው የህዝብ ተቃውሞና ጥያቄ ለማምለጥ ሲሉ መጨረሻ የሌለው ስብስባና ኮንፈርሰ በማካሄድ ከፖለቲካዊ ንግድ ሊያልፍ የማይችል ኑዛዜ በማሰማት ላይ  መሆናቸውን እያየን እና እየሰማን እንገኛለን።  
     በመሆኑ  ህወሓት እንደተለመደው  በዚህ ሳምንት በራሱ ላይ ተነስቶ ያለው  ሃይለኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ለማዳፈንና   የህዝብን  አስተሰሰብ  ለመጠምዘዝ ሲል ሲቪል ሰርቫንት በሚል ስም  ኮንፈርስ  በዚህ  ሳምንት ኣካሂደዋል። 
    የህዝብ ችግር ሊፈታ የሚችለው ግን ስብሰባዎችን  በማራዘም  ሳይሆን  ከታች እስከ ላይ ያሉትን አመራሮች፤ ሰራተኞችና   ሲቪል ሰርቫንት ከጉቦና ከብልሹ አሰራር  ነፃ ሆነው  ለህዝብ በቅንነት በማገልገል በወቅቱ ተገቢ መልስ  ሲሰጡና  በእኩልነት  ሲያገለግሉ ብቻ ነው። 
  ሰለሆነ  በህወህት  ኢህአዴግ  በመከበር ላይ ያለው  የሲቪል ሰርቫንት ቀን  ለማስመሰል፤  ለጥቅምና  ለባለስልጣኖች እድሜ ማራዘምያ ከመሆን አልፎ  የሚያመጣው መሰረታዊ  ለውጥ የለም ። 

No comments:

Post a Comment