Thursday, July 14, 2016

በአዲስ አበባ ከ20 ዓመታት በላይ ሲኖሩበት የቆዩትን ቤት ልቀቁ በማለት በአስቸጋሪ ሁኔታ በአፍራሽ ግብረ ሃይል ትዕዛዝ መውረዱና መፍረሱ አግባብነት የሌለው መሆኑ እየተገለፀ ነው።



በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች ስርዓቱ በአሁኑ ጊዜ እየወሰደው ያለው የማፍረስ እርምጃ ተገቢነት የለውም ሲል መኢአድ የገለጸ ሲሆን ሐምሌ 5ቀን 2008ዓ.ም ዜጎች ለረጅም አመታት ሲኖሩበት የቆዩት ቤታቸው ፈርሶ ለጎዳና ተዳዳሪነት  መጋለጣቸውን መኢአድ በጥብቅ እንድኮነነው በአወጣው መግለጫ አስታውቋል።

   መኢአድ ጨምሮ ለወደመ ንብረትንና ህይወት ምክንያት የሆኑ በመንግስታዊ ኃላፊነት ያሉ ባለስልጣናት ወደ ህግ እንዲቀርቡና ቤታቸው ፈርሶ በየጎዳናው የሚገኙ ወገኖች ደግሞ በአፋጣኝ ምግብና መጠለያ እንዲሁም ሌሎች አቅርቦት እንዲሟላላቸውና በተለያዩ አካባቢዎች እየተደረገ ያለው የቤቶች መፍረስና ውድመት የዜጎች መጎሳቆል እንዲቆም መኢአድ አስጠንቅቋል።

   በተጨማሪም በርካታ ወገኖች እየገለፁት እንዳሉ ቤቶች እየተሰሩ ባለበት ጊዜ መንግስት አስቀድሞ ማገድ እየነበረበት ለረጅም ጊዜ ዜጎች ሲኖሩበት የቆዩትን ቤታቸውን አሁን እንዲፈርሱ ማድረግ ከአንድ ህዝብ አስተዳድራለሁ የሚል መንግስት ሊፈፅመው የማይችል እርምጃ ነው በማለት እየገለጹ ሲሆን በዚህ ተግባር ደግሞ ከላይ እስከታች ያሉት የስርዓቱ ባለስልጣናት ተጠያቂ እንደሆኑ ተገልጿል።

No comments:

Post a Comment