ግብር መክፈል የማይቀር የሁሉም ዜጋ ሃገራዊ ግዴታውና ሃላፊነቱ መሆኑ ለሁሉም
የሚያረዳዳ ነው። ምክንያቱም የአንዲት ሃገር ልማትና እድገት የሚሳለጥ
ከዜጎች በሚገኘው ግብርና ቀረጥ ሰለሆነ፣ በመሆኑም የሚሰበሰበው ግብር ተመልሶ በመሰረተ ልማትና እድገት ግንባታ እንዲሁም ፍትሃዊ ተጠቃሚነት፤ ግልፅነትና ተጠያቂነት የመሳሰሉ መሰረታዊ
ነጥቦች የሚረጋገጡትም ነፃ የፍትህ ስርአት እንደ ቁልፍ አሰራር ተወስዶ ህዝቡ የፍትህ አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችል አሰራር ሲኖር
ብቻ ነው።
ይሁን ኣንጂ ፍትህና ዴሞክራሲ የሚጠየፍ የአናሳዎች
ጥቅም ስልጣን ለማስጠበቅ የቆመ ስርአት ፍትሃዊነት ያለው የዜጎች
ግብር አከፋፈል ይፈጠራል ብለህ የሚጠበቅ አይደለም።
በዚህ መሰረትም በህዝብ ልጆች ጀግኖች መስዋእት
ተንተርሶ ስልጣን የተቆናጠጠው የጥቂቶች ስብስብ ጉጅሌ ኢህአዴግና አጋር ድርጅቶችሁ ስናይ የሳልጣን ወንበር ከተቆናጠጡበት እለት
ጀምረው እስከ አሁን ድረስ ዘላቂነት ያለው የግብር አሰባሰብ ስርአት ሳያመቻች ፍትሃዊነት የጎደለው ከልክ በላይ ግብር ከድሃ ህዝብ እየቀማ ለግል ኪሱ መሟያ
እያደረገው መጥቷዋል አሁንም እየቀጠለበት ይገኛል።
የኢህአዴግ መሪዎች ስርአት ያለው የግብር አሰባሰብ
ባለማከናወናቸው ምክንያት ደግሞ በዜጎች ላይ ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን
የግብር መጠን ክፈሉ እየተባሉ ትእዛዝ ሲወርድባቸው ግብር ከፋዩም በበኩሉ ይህንን የኔ አይደለም ስረቼ ያገኘሁት ይቅርና ንብረቴን
ተሽጦም ለግብር መክፈያ የሚሆን የለኝም በማለት ሲያለቅስ ጥያቄ ይሁን አቤቱታ በሚያቀርብበት ጊዜም መፍትሄ የሚሰጥ አጥቶ እያጉረመረመ
እንዲከፍል እያደረጉት መጥቷል አሁንም እየቀጠሉበት ይገኛሉ።
በመሆኑም ቀዋሚና ተንቀሳቃሽ ነጋዴና የሽቀጥ
እንዲሁም የድርጅት ባለቤቶች ከልክ በላይ ግብር እንዲከፍሉ የሚወርድባቸው ታዛዝ አልከፈልክም ተብለው ድርጅታቸውን ሲዘጋባቸው ብሎም ጠቅልለው ሳራቸው አቁሞ
ትስፋ በመቁረጥ ወደ ስደት ሲያመራ በሳህራ በርሃና በባህር በህይወቱ ወድቆ የሚቅር ወገን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ነው።
ፍትሃዊነት የሌለው በዜጎች ላይ የሚጫን ከልክ
በላይ የመንግስት ግብር ለተቃወመና በዴሞክራሲ መንገድ መብቱ ለጠየቀው ህዝብ ፀረ ልማትና የተገኘውን እድገት የሚያደናቅፍ በሚል
ስም እየተጠመቀ በሃገሩ ላይ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየተቆጠረ እንዲኖር ተፈርዶበት ይገኛል።
በዚህ አመት በመልካም አሰተዳደር ስም እስከ
አሁን እየተካሄደ ያለውን አስመሳይ ኮንፈረንስና ተከታታይ ስብሰባዎች የችግሩን ሰለባ እየሆነ ያለውን ህዝብ ከልክ በላይ ግብር በግዴታ
እየከፈልን ነን፤ በግምት የሚከፈል የገቢ ግብር ለሙስና የሚያዳርግ ስለሆነ በሙስና ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት የሚያውቁትን ሰው
እንደ ፍላጎታቸው ሲቀኑስለት የማያውቁትን ሰው ደግሞ ግብር እየጫኑበት ነው ያሉት። ለዚህ ሁሉም ለመፍታት ፍትሃዊነትና ስር አት
ያለው የግብር አሰባሰብ ሂደት ይኑር በለው የሚጠይቅና የሚነቅፍ ቢኖርም እንዃ አሁንም ከተራ ፕሮፖጋንዳና ሸቀት የዘለለ መሰረታዊ
መፍትሄ ሊያመጣ አልቻለም።
ስለዚም በዚህ አመት ከሃምሌ አንድ የሚጀምር
የገቢ ግብር ከዜጎች ደግሞ እንደልማዱ ፍትሃዊነት የጎደለው የግብር አሰባሰብ በሃይል እንዲቀማ ሊገደድ ነው። ምክንያቱም ፍትህ የሚጠየፍ
ስርአት ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ሊያረጋገጥ ስለማይችል።
No comments:
Post a Comment