Friday, July 15, 2016

የኢትዮጵያ ችግር በሚድያ ጭሆት አይፈታም!



 በዚህ ሳምንት የህዝብና የአገር ጠብቃናና ጥቅም የሌላቸው የገዥው ስርአት  ሚድያዎች  ሰፊ ሽፋን በመስጠት  ሰለ የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስተር  ቤንያሚን ናታንያሁ ከሰሃራ በታች ላሉት የአፍሪካ አገሮች  ጎብኝተው  በመጨረሻ  ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉት  ጉብኝት ምክንያት በማድረግ ሚድያዎች እየተቀባበሉ ሲያወሩት መሰንበታቸው የሚታወቅ ነው።
    ጠቅላይ ሚንስተሩ በስማዊው የወያኔ ኢህአዴግ  ፓርላማ  ፊት  ተገኝተው ከሰጡት ሃሳብ ኢትዮጵያና  እስራኤልን በታሪክ   ለረጅም ግዜ  የተሳሰሩና  እንደዚሁም  ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት   በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉ አገሮች ናት በማለት በጭብጨባ ታጅበው    የኢህአዴግ ባለ ስልጣናት  ያጠነጠኑትን  ተንኮል   በመድገም ቀጥለውም መንግስታቸው በኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ ንዋይ በማፍሰስ  ኢንቨስት እንደሚያደርግና ዳግመኛ ወደ ኢትዮጵያ  የመምጣት ፍላጎት እንዳላቸው  መገለጫ  ሲሰጡ ተሰምቷል።  
   ይህ ምናልባት ኢትዮጵያና  እስራኤልን በሃይማኖት የተሳሰሩና   ለረጅም ዘመናት  የቆየ ታሪክ እንዳላቸው የማይካድ እውነት ነው፣. እንደዚሁም ለመጀመርያ ጊዜ ከእስራኤል ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ ጠቅላይ ሚንስተር አንዱ ተብለው ሊገለፁ  ይችሉ ይሆናል ቢሆንም እዚህ መነሳት ያለበት ጉዳይ ባለፉት 25 ኣመታት መምጣት  ያልቻሉ ኣሁን የመጡበት ምክንያት ለምንድ ነው ተብሎ ሊታሰብበትና ማስተዋል  የሚገባው ነጥብ ነው። 
    የዚሁ አይነት  የውጭ መሪዎችን እድሜ በማድረግና በመጋበዝ  በሰጠናችህ የይምሰል ሪፖርት እድገታችንን ኣሳውቁልንና   በአገርትዋ እንደፈለጋችሁ መዋእለ ንዋያችሁን ለማንቀሳቀስ ትችላላችሁ  በሚል የተምበርካኪነት አካሄዳቸው አዲስ  ሳይሆን  ረዥም ጊዚያቶችን ያስቆጠረና ለውስጣዊ ውጥረታቸውና ጭንቀታቸው  ለመሸፈን ሲሉ በሚድያ ሰፊ ሽፋን በመስጠት  የህዝብን ስነ ኣእምሮ መጠምዘዝ   የከሰረ የኢህአዴግ ባለስልጣኖች ፖለቲካ መሆኑ ጥያቄ የሚያስፈልገው ጉዳይ ኣይደለም።   
  ይህ  የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስተር  ወደ  ኢትዮጵያ መምጣት ደግሞ ልክ እንደ ባራክ ኦባማ  ለተወሰኑ ቀናቶች  በሚድያ  ትኩረት በመስጠት እንዲሰራጭ ማድረግ ለግዝያዊ ውጥረታቸው አቅጣጫውን ለመቀለበስ  የታለመ ውዲት ከመሆን ኣልፎ ፋይዳ የሚገኝበት ኣይደለም። 
   ምክንያቱም አገራችን ኢትዮጵያ የኤኮኖሚ እድገትዋ ከኢትዮጵያውያን በላይ የሚያውቃት ሌላ ኣካል የለም፣ የኢህአዴግ  መሪዎች አድጋችሃል  ሰልጥናቹሃል  ቢሉንም እንኳ ምላሹ ግን ኣይደለም  ነው፣ ምክንያቱ የኑራችን ችግር የምናውቀው  እኛው ራሳችን  ነን  ፣ እናንተ ባለ ስልጣኖች   በሙስና  አድጋቹሃል  እኛ ግን ኑራችን ወደ  ኋላ እያንቆሎቆለ  በመውረድ ላይ ይገኛል  ስላልናቸው  ብቻ  የውጭ መሪዎችን  ጠርተው  መሰክሩልን ማለታቸው በህዝብ ማላገጥ ነው።     
  ከዚህ ባለፈ የኢህአዴግ ባለስልጣኖች እንደልማዳቸው ያለ  ተጠያቂነት የህዝብና የአገር ሃብት የሆነውን የኢትዮጵያ ተፈጥሮአዊ  ፀጋዎች ማለት ሰፊና ድንግል እርሻ መሬት እንደዚሁም ህዝባችን  ለአመታት ከነበረበት መሬቱ  እያፈናቀሉ  በኢንቨስትመንት ስም የውጭ ባእዳውያን ዜጎች እንደ ፍላጎታቸው በርካሽ ዋጋ   ሲንደላቀቁበት ዜጎች ደግሞ በርካሽ ዋጋ በውጭ ድርጅቶች  እንዲሰሩና  ዘመናዊ ባርነት የሚፈቅድ በመሆኑ  ወደ ከፋ ድህነት  የሚያሰገባ ውሎችን ከመጋረጃው በሰተ ኁላ ስላለ ነው።
   ህዝባችን በአሁኑ ሰአት በኢህአዴግ  መሪዎች ፀረ ህዝብ ተግባር   የታለመ  ተንኮል  ወድቆና ፍትህ አጥቶ  ሰብአዊ  ርህራሄ በሌላቸው  ከውስጥና ከውጭ በመጡ ሃይሎች  እለታዊ  ኑረው እያታመሰና   በማሃል ሜዳ እየተደበደበ ሂወቱ እያጣ ይገኛል።
  በመሆኑም ውስጣዊው ውጥረት መፍተሄ ሳታበጅ  ለውጭ  አገር መሬዎች እንዲናገሩ ወደ መድረክ  መጋበዝ  ጊዚያዊ  የፕሮፖጋንዳ  ንግድ ከመሆን አልፎ የሚያመጣው ትርፍ እንደሌለ ሊታወቅ ይገባል።   

No comments:

Post a Comment