Saturday, July 23, 2016

በሳምረ ሳሓርቲ ወረዳ ከፍተኛ የመጠጥ ውሃ እጥረት ስላጋጠመ፣ ነዋሪዎች ይፈታልን በማለት አቤቱታቸውን በማሰማት ላይ እንደሚገኙ ታወቀ።



  በመረጃ ምንጮቻችን  መሰረት።- በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ሰሓርቲ ሳምረ ወረዳ ለረጅም ጊዜ  የውሃ እጥረት ተከስቶ ባለመፈታቱ፣ ነዋሪዎች “ እስከ መቸ ድረስ ነው በውሃ  ጥም የምንሰቃየው መንግስት የለም ወይ” በማለት ለሚመለከታቸው አካላት አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም እንኳ፣ መፍትሄ ሊያገኙ ስላልቻሉ እስከ አሁን ድረስ በውሃ እጥረት እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል።
   በወረዳው በ2008ዓ/ም በክልሉ መንግስት 17 ሚልዮን ብር ወጭ የተደረገበት የውኃ ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ የውሃ ቧንቧዎች በወረዳው ይተከላሉ ቢባሉም። በተባለው ጊዜ ሊሳለጥ ስላልቻለ መንግስት በቅርብ ጊዜ ተጨማሪ 2.3 ሚልዮን ብር በጀት ለችግሩ መፍትሄ  አወጣሁ ቢልም፣ ለፕሮጀክቱ ሳይውል የአካባቢው ባለ ስልጣናት ከፕሮጅክቱ አስተባባሪዎች ጋር በመሆን ስላጠፋፉት የወረዳው ነዋሪዎች በተለይ ደግሞ የሳምረ ከተማ ነዋሪዎች በመጠጥ ውሃ እጦት እየተሰቃዩ መሆናቸውን መረጃው ጨምሮ ገልጿል።     
   በዚህ ደግሞ የክልሉ አስተዳደር የበጀት ቁጥጥር ድክመት እንዳለውና ለራሱም በሙስና ተዘፍቆ እንደሚገኝ የገለፁት ነዋሪዎች፣ በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ የወረዳው አስተዳዳሪዎች ጥራቱን የጠበቀ ውሃ እናቀርብላችኋለን በማለት ከአንድ ሚልዮን ብር በላይ ከህዝቡ በማውጣት ለሳመረ ከተማ በቦቲ ውሃ እያቀረቡለት ቢሆኑም እንኳ። ውሃው ግን ጥራቱን ያልጠበቀና በቂ እንዳልሆነ የሳምረ ከተማ ነዋሪዎች በምሬት ይናገራሉ።     

No comments:

Post a Comment