Saturday, July 30, 2016

በአፋኙ የኢህአዴግ ስርአት ላይ የሚቀጣጠል ቀጣይነት ያለው ትግል



   ኢህአዴግ በሚል ስም በስልጣን ላይ እየቀጠለ የሚገኝ ገዢው ስርአት ለሩብ ክ/ዘመን የሚያክል በስልጣን ላይ መቆየት የቻለ በመላው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ፍላጎት ሳይሆን በጠመንጃ ኃይል  እንደሆነ ጋህድ እዉነት ነው።
    ይህ አረሜናዊ ስርአት ከመጀመርያ ጀምሮ በመስዋእትና በስንክልና የተገኘው ድል ተንተርሶ የተቆጣጠራት ወንበር ከድል በኃላ በግልጽ  ካሳየው  ክህደት  ኣንስቶ   ህዝባችን ስርአቱ  የጥቂቶች ፍላጎትና ጥቅም ስብስብ  መሆኑ ለማወቅና በላዩ ላይ ለመነሳት ግዜ ኣልወሰደበትም።

   በመሆኑም ህዝባችን ለእኩይ ተግባሮቹና ክዳት በግልም ይሁን በቡዱን ሆኖ ህገ መንግስታዊ መብቱን ለማግኘት  በአደባባይ ወጥቶ ተቃውሞና ጥያቄዎችን ላሰማ ወገን በጥይት ተመቶ ሂወቱ ሲያልፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች ደግሞ  በውሸት በመወንጀል  በየጊዜው እስር ቤት እየታጎሩ እንደዚሁም በሚድያዎች ህዝብን ለማደናገር በማለት የተለያዩ ስሞችን በመሰየም ያልሞከረው ፈተና የለም ቢባል ማጋነነ ኣይደለም።    
  
   በተጨማሪም በዚህ ሳምንት በሰሜን ጎንደር የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞና የጠፋው የሰው ህይወት መንስኤው ለአመታት  ህዝብ ሲያነሳቸው የነበሩ  የዴሞክራሲ፤ የፍትህ፤ የሰላምና የልማት  ጉዳይ መፍትሄ ከመስጠት  ይልቅ የፀጥታ ሃይሎችን በማሰማራት ጥያቄዎችንና ኣቤቱታዎችን   ለሚያቀርቡ  ወገኖች ኣነሳሾች፤ ፀረ ልማትና   ህገመንግስቱን ተፃራሪ እየተባሉ ሲደበደቡና ቢጠፉም እንኳ  ያለ መፍትሄ  ከየቤታቸው  እየተፈለጉ  ቢታሰሩም    ጭቆና  የወለደው የህዝብ ጥያቄ ፈነዳ እንጂ ሊገታ ኣልቻለም።    
 
 ይህ በመካሄድ  ላይ ያለውና በኢህአዴግ ላይ የተነሳው ህዝባዊ የተቃዉሞ ትግል የሚሞገስ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በጠባብ ኣመለካከትና ጥላቻ የተነሳ  በአንድ ብሄር ያነጣጠረ  መነሳሳት እያደርግክ የሚጠፋ የሰው ሂወትና ንብረት አሰቸኳይ መፍትሄ  ሊደረግለት  ይገባል።
   በስርአቱ በኩልም በሰሜን ጎንደር የተነሳው  ግጭት  የጠፋው ሂወትና የወደመው ንብረት ኣስመልክቶ  ሲሰጥ የሰነበተው መግለጫዎች  በመጀመርያ በኢትዮጵያ የመንግስት ኮሚኒኬሽን  ፅህፈት ቤት የተሰጠ ሲሆን  በሁለተኛ ቀን ደግሞ ከፌደራል ፖሊስና ከብሄራዊ ደህንነት መረጃ ክፍል በተሰጠ መግለጫ  ህዝብ ለማደናገርና ለማምሰል በሚስችል ያለርህራሄ  በፈደራል ፖሊስ በግፍ ሂወታቸው ያለፈ የጥቂት ታጋዮችን  ምስሎችን በተለቭዥን በማሳየትና የተጠለፈ  ድምፅ ደጋግሞ ለማሰማት ተገደዋል።     
  ይህ ደግሞ  በማወቅ ሳይሆን  ከውጥረት  ተነስቶና ካለፉት  ገሃድ የሆኑት ልምዶቹ በተየያዘ  ጨቛኙ ቡዱን በመሆን ህዝብ በሚገባ ስለሚያውቀው  ሁሉም  የትግል አይነት  በመከተልና  በማቀጣጠል  ላይ ይገኛል።      
   ምክንያቱ ህዝብ ፋሽስታዊ የደርግ ስርአት ድል ሊመታ የቻለው በሜዳ  መንገድ  ተጉዞ ሳይሆን  በራሱ ላይ እጅግ ብዙ  ግፎችን  አልፎና  ወንበዴና  የወንበዴ ቤተሰብ  እየተባለ  ቁም ስቅል አይቶና  ምርጥ ልጆቹ  የከተማ የገጠር የወንበዴ ኣባላት ናችሁ እየተባሉ   በጎደና እየታደኑና  አለም በቃኝ ወደ ተባለው እስር ቤት ተወርውረውና ለከፋ ስቃይ መከራ ሲወርድባቸው  የድርጅታቸውን ሚስጥር ኣሳልፈው ላለመስጠት  ሂወታቸው ስታልፍ እንደዚሁም ደግሞ  በየመንገዱ   በወላጆቻችው  ፊት  እየተገደሉ    የጥይት ራት ሲሆኑ   በውስጡ ደም እያነባ  ከዚሁ ስቃይ ለመገላገል ልክ ቆፎን እንደተናካ ንብ  ሆ ብሎ ወደ ትግል መጉረፉ  የቅርብ ጊዜ ታሪክ   ነው።     
    ምክንያቱ ንፁሃን ታጋዮችን  ገድለህ የተለያዩ  የውሽት ደባ   በመፈፀም ህዝብን በአፈና መርበብ አስገብተህና ኣስረህ ነገሮች ሊቃኑና በስልጣን የሚያስቆይ  ቢሆን ፋሽታዊው የደርግ ስርዓት  ከዚህ  የተለየ  ባህሪ ምን ነበረው  የሚል  ጥያቄ  ልታነሳ   የሚያስገድድ  ነው፣ ስለዚህም   በአፋኙና በአረመኔው  የኢህአዴግ ተግባሮች ወደፊት የሚቀጣጠል  ትግል እንጂ  የሚገታ  አይኖሩም።           



No comments:

Post a Comment