Sunday, August 14, 2016

በአዲስ አበባ ከተማ በኢንዲስትሪ ዞን የሚገኘው መሬት ለጭረታ ሰለቀረበ ተቃውሞ መነሳቱ ታወቀ።



   ከ400 በላይ ኩባንያታት የኢንድስትሪ መሬት እንዲሰጣቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት  የአዲስ አበባ የመሬትና የልማት ማኔጅመንት ፅህፈት ቤት ደግሞ በኢንዲስትሪ  ዞን  የሚገኘው  መሬት ለጭረታ  ሰለቀረበ  በዚህ የተቆጡ ወገኖች ቅሬታቸውን በማቅረብ ላይ መሆናቸው ተገለፀ፣  
   የከተማ  መሬት  በሊዝ  የመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004   የኢንዲስትሪ መሬት በምደባ እንደሚሰጥ  የሚደነግግ ሁኖ የከተማው ማኔጅመንት ፅህፈት ቤት  በ22 ዙር ጭረታው  በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ላፍቶ  በወረዳ 12 የሚገኝ መካኒስ ለቡ የተባለ  የኢንዱስትሪ ዞን  መሬት  በእሁኑ ግዜ ወደ ጭረታ የቀረበ ሲሆን የዚህ ኣይነት አሰራር  የሊዙን አዋጅ  ለማስፈፀም  የወጡትን ድምቦችና መመርያዎች  የሚቃረን ነው በማለት  ለኢንዱስትሪ መሬት  እንዲሰጣቸው  ጥያቄ ያቀረቡ ዜጎች ገለፁ፣    
  በሊዝ አዋጁ መሰረት የከተማው መሬት  ለተጠቃሚዎች  በሁለት መንገድ  የሚተላለፍ ሲሆን  በመጀመርያው በጨረታ  ሁለተኛው ደግሞ በምደባ ሲሆን  በሊዙ አዋጅ አንቀፅ 12  ለማኑፋክቸሪንግና ለኢንዱስትሪ  መሬት በምደባ  እንደሚተላለፍ  በግልፅ ሲደነግግ    በዚህ  በሁለቱም ድንጋጌዎች    መሰረት በማድረግም  ለኢድስትሪ የሚሆን መሬት እንዲሰጣቸው ጥያቄ  ያቀረቡ   ዜጎች  ስር አቱ ለኢንድስትሪ የሚሆን መሬት ለጭረታ  በመቅረቡ ቅሬታቸው በመግለፅ ላይ መሆናቸው ተገለፀ ።



No comments:

Post a Comment