Friday, February 17, 2017

ለሚረግጡት ረመጥ መሆኑን ያስመሰከረ ህዝብ!!



ይህ ማንነቱንና ክብሩ የማይደፈር ህዝብ በጥቂት በግዜው ከዳተኛ ግለሰቦች ሰብዓዊነቱ ሊነጠቅ ወይም ሊደፈር ታሪኩና የጥንት አባቶቹ ታሪክ ፍፁም አይፈቅድለትም። ምክንያቱም ማን መሆኑንና ከማን እንደተፈጠረ ራሳቸው በእጁ እየተመገቡ አድገው አሁን ህዝባዊ አደራን እና ሃላፊነታቸውን በመተው በጊዜያዊ ስካር ያበዱ መሪዎች ይህንን ህዝብ ማንነቱን ረስተው ሊበድሉት ቢፈትኑም ለጭቆና ወግድ ካለ ሊገታ የማይችል ማዕበል ስለሆነ አንድ ቀን እንደሚጠርጋቸው እነሱም በሚገባ ያውቁታል።
ሐቁ ይህ ከሆነ ለዚህ ድንበር የለሽ የሆነ የእነዚህ መሪዎች ግፍና በደል በላዩ ላይ እየተደጋገመ እንዲቀጥል የሚታገስ ህሊና እንደሌለው ይህ እየሰማው ያለው የእምቢተኝነት ድምፅ በቂ ማስረጃ ነው።
ሆኖም ግን ይህ ከህዝብ ተነጥሎ ያለው ስርዓት አሁንም  በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚወስደው የቀቢፀ ተስፋ እርምጃዎች የአረመኔያዊ ተግባሮቹ ማሳያ  እያወረደ ቢሆንም፣ ሆኖም ግን ይህ ለግፍና ጭቆና ወግድ እያለ በሱሪው ስርዓቶችን እየወረወረ የመጣ ህዝብ ግን አሁንም ፊት ለፊት በመጋፈጥ ላይ ነው ያለው።
ስለሆነም እነዚህ ጥቂቶች መጥፎዎች በእድሜ ስልጣናቸው ሙሉ በወገናቸው ላይ ሲፈፅሙት የቆዩትና ያሉት ማንኛውንም አይነት በደሎች ዛሬ የሚረግጡት መሬት ረመጥ ስትሆንባቸው ከአደጋ ሊያድናቸው የማይችል ጊዜያዊ ፈጠራዎች ለማዳሰስ ተገደዋል።
ይህ ሲረግጡት ረመፅ የሆነ ህዝብ ግን በማንኛውም አይነት ታምር በእነዚህ አንድ ግዜ ከህሊናው ፍቆ የወረወራቸው ደመኛዎቹ ዛሬ ላይ ደርሰው የህዝብን ቁስል ሊያድን የሚችል መድሃኒት ሊያመጡልኝ ይችላሉ የሚል ተስፋ የለውም። ምክንያቱም ኢህአዴጋውያን የስልጣን ስስት እንጂ ህዝባዊ አላማና ጥቅም አስቀድመው በሱ ተገዥ ለመሆን ህሊናቸው አይፈቅድላቸውም። ይህ እንደዚህ አይነት እውር የስልጣን ስግብግብነትና ስስት የተጠናወተው ስርዓት ደግሞ መወገድና መወቀስ ስላለበት ህዝብ ደግሞ በሁሉም የአገሪቱ አቅጣጫ ለዚህ የህዝብ ደመኛ የሆነ ስርዓት ለማስወገድ በመረባረብ ላይ ይገኛል።

ሆኖም እነዚህ የህዝብ ውክልና የራቃቸው ሴረኛዎች ግን ዛሬም ለይምሰል ህዝብ ምን እንደሚፈልግ መድረኮች እየከፈቱ በመጠየቅ በል ተናገር እያሉ ምርጫውንና ያለውን ቁስልና ጥላቻ ከተረዱ በኋላ፣ አንፃራዊ መልስ ሊሰጡትና ለምን ከእነሱ ፍላጎትና ምርጫ እንደወጣ በተለያዩ ስሞች ሲጠምቁት ነው እየታዩ ያሉት።
ይህንን በምሳሌነት አስደግፎ ማንሳት ይቻላል። ማለትም ሌላው እንዳለ ሆኖ ይህ በአምባሰነይቲ ህዝብ በአስተዳደር እጥረትና በመሰረተ ልማት እጥረት መሰረት በማድረግ ከ20 ዓመታት ያህል በአቅራቢያው የሚተዳደርበትና ፍትህ የሚያገኝበት ሂደት እንዲኖር ያለእረፍት ለሚመለከታቸው አካላት አቤቱታውን እያቀረበ እንደመጣና እንዳለ የሚታወቅ ነው።

ይሁን እንጂ ይህ ወረዳችን ይመለስ በሚል ጥያቄ ያስነሳውን የደርግ ናፋቂዎች፤ አነሳሾች፤ የመንግስታችንና የህገመንግስታችን ፀረ ልማት እየተባለ ስም ሲለጠፍበትና ከጎረቤቶቹ ጋር በጥርጣሬ አይን ሊታይ እንደቻለ ህዝብ እየሰማው ያለ ሐቅ ነው። ህዝብ ግን ትክክለኛውን ሊደግፍ ችግርንና ሊያገኘው የሚገባውን ጥቅም ደግሞ ደረሱልኝ ወይም ደግሞ ተው ሊል የእርሱ ድርሻ ነበር።
ይሁን እንጂ የዚህ መፍትሄ ከሚሆን ይልቅ የችግሩ አካል እየሆነ እየሄደ ያለው ገዥው ስርዓትም ይሁን በትግራይ ያለው ጉጅሌ በሚያካሂዳቸው ተግባራዊነት የሌላቸው መድረኮች ተከትሎ የሚገባቸው ቃል ኪዳኖች መልካም ተግባር መጠበቅ እድሜ ስልጣኑን ከማስረዘም አልፎ የሚፈጥረው ታምር አይኖረውም።
ምክንያቱም አሁን ይህ ፈንቅሎ እየወጣ ያለው የህዝባችን ክፋትና ምሬት የትግሉ ውጤት እዲሁም ከስርዓቱ ቁጥጥር ስር ውጭ ሆኖ በከፋ ሁኔታ ደርሶ እንዳለና በዚህ ልክ ደግሞ ረመጥ መሆኑን ረስተው ሊረግጡት የወሰኑ መሪዎችን ዝም ብሎ የሚያይ ወይም ተረግጦ ዝም የሚል ሳይሆን ለሚረግጡት ረመጥ መሆኑን አረጋግጧል።

No comments:

Post a Comment