Tuesday, July 25, 2017

ጠባሳ በመጉዳት አይድንም  ባለፉት ቅርብ አመታት በተለይ ደግሞ የጥቒቶች ጥቅም ለመጠበቅ አልሞ በማስተር ፕላን ስም በአዲስ አበባ የወጣ አዋጅና ባስከተለው መዝዝ፣ ህዝብ ያማይወክለው መሆኑንና ወደ አደባባይ ወጥቶ ተቃዉሞዉን ሲያሰማ የፅጥታ ሃይሎች ለሚነሳው ተቃዉሞ በብረት ለመግታት በመኮሩበት፣ ድንገት ከዉሱን ቦታ ተነስቶ ወደ ሁሉም  ገጠርና ከተማ የኦሮሞ አከባቢዎች እየተቀጣጠለ በመሄድ በርካታ ሂወት አጥፍቶና አሰቃይቶ ሲያበቃ
  ለአመታት መፍትሔ ያላገኙ ሲነሱ የቆዩ የማንነት የአዋሳኝ ጥያቄዎችና ግጭቶች በተያያዘ በአማራ ክልልም ተቐጣትሎ ጎንደር ከተማም በሓምሌ 5. 2008 ዓ.ም እንድትናወጥ አድርጓታል። በዚህ ምክንያትም በርካታ የሰው ሂወት ጠፍተዋል በሚልዮኖች የሚገመት ብር ወድመዋል ብሄር መሰረት ያደረገ ጥቓትም ተፈፅመዋል።
 ይህ የወለደው ደግሞ በህዝቦች መካከል ከባድ ስጋትና መጠራጠር ፈጥሮ ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሰው ሰርተው የሚኖርበት ዕድል እየጠበበ መጥተዋል።
  ይህ ብቻ ሳይሆን በደቡብ ክልል ጌዶ ዞን በአራት ወረዳዎችና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች በተነሳ ብሄር መሰረት ያደረገ ግጭት ከ34 በላይ የሰዎች ሂወት አጥፍተዋል። የአካልና የንብረት ዉድመት እንዳስከተለም ይታወቃል።
በሶማለየና ኦሮም ፣ በአፋርና ኣማራ እንዲሁም  በትግራይና ኣፋር ክልሎችም በአዋሳኝ ቦታዎች ምክንያት እየተነሳ የሰዎች ሂወት እየቀጠፈ ለቐጣይም መጥፎ ታሪክ እየተወ ቀዋሚ መፍትሔ አጥቶ እየቀጠለ እንደሚገኝ የሚረሳ አይደለም።
በሁሉም አቕጣጫዎች በኢህአዴግ መጥፎ አስተዳደር የተማረረ ህዝብ እንገቱን አዝሮ ጭቆና አንቀበልም፣ለብዝበዛ እጃችን አንሰጥም የሚል ወኔ አድሮበት ለመብቱ እንዲቆም ተገድደዋል። ይህ የህዝብ ቁጣ የሚያድን መልስ ሳያጋኝ ተግባራዊነት የሌላቸው የተለያዩ ማደናገርያ ፈጠራዎች እየተበራከቱ እንዲሄዱና ለሚድያ ሸፈነ እንዲዉሉ እያደረጉ ነው።
በድምር ሲታይ ህዝብና አገር ወክሎ እያስተዳደርኩ ነኝ የሚል ስርዓት ከህዝብ የሚደርሰው እጣ በስልጣን የሚያቆየው ሁኔታ አልነበረም።በአገራችን ፖለቲካዊና ማሕበራዊ አለመረጋጋት በመፍጠሩ ብህዝብብ ላይ ደግሞ ከፍተኛ ማሕበራዊና ስነ ልቦናዊ ጫና አስከትሏል።
ስለዚህ ለህዝብ ጥያቄ ትኩረት ተደርጎበት ዘላቂ መፍትሔ መደረግ ነበረበት እንጂ በላዩ ላይ የጥፋት ደመና ተንጃብቦበት በጢቆቶች ሰንሰለት መግባት አልነበረበትም።  
ይህ ስንል ከስምንት ወር በፊት የኢሪቻ ባህላዊ በአል ለማክበር የተሰበሰበ የኦሮሞ ህዝብ በተፈጠረ ሁከትና ድንግርግር ተከትሎ የጠፋ የንፁሃን ዜጎች ሂወትና ያስከተለው የህዝብ ቁጣ ምን አይነት ሁኔታ ተፈጥሮ እንደነበረ ከማንም የተደበቀ አይደለም።
ይህ ደግሞ መፍትሔዎች ከመፈለግ፣ አስቸካይ የግዜ አዋጅ ተብሎ ዜጎች በተቓዉሞው እጅ ነበራቹ እየተባሉ በኮማንድ ፖስት እየተፈለጉ ወደ እሱር ቤት እንዲገቡና እንዲሰቓዩና ከአገራቸው እንዲሰደዱ ተደርገዋል።
  በዚህ መንገድ ለ6 ወራት ተመኩሮ መፍትሔ እንዲሆን ባለመቻሉ እንደገና ለሁለት ወራት ተራዝሞ ሲያበቃ በዚህ ሳምንት ደግሞ የመከላክያ ሚኒስተር በዋናነት ለጋዜጠኞች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አዋጁ ከክልል መንግስታትና የፀጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ዉጭ በማይሆንበት ሁኔታ በመድረሱ ከ ፌደራል ወደ ክልል አስተዳደሮች ይዞራል ሲል ገልጿል።
ስለዚህ የህዝብና የአገር በሰላ እንዲታከም ከሆነ ለተነሳ የህዝብ ጥያቄና ፍላጎት መሰረት ያደረገ መፍትሔዎች ማስቀመጥና መስራት እንጂ በኣንድ ጎኑ የጎተመ ስለትህ ቀይረህ  በመሞረድ ለህዝብ እንድትጨቁን መፈለግ መሞከር መፍትሔ አይደለም
   

No comments:

Post a Comment