Friday, February 16, 2018

በደቡብ ክልል በከምባታ ዞን ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ ሲደረግ ዋለ።



  የኦሮሞ ወጣቶች (ቄሮ) ለአማራ ክልል ወጣቶች (ፋኖ) እና ለደቡብ ክልል ወጣቶች ለ3 ቀናት የሚያደርገውን ተቃውሞ እንዲቀላቀሉት ባቀረበው ጥሪ መሠረት በጎንደር የተወሰኑ ከተሞች (ዳባትና ደባርቅ) እና በሌሎች ኢንተርኔትና ስልክ በመቋረጡ የተነሳ ያልተዘገቡ የአማራ ክልል ከተሞች ሕዝባዊ ተቃውሞ ሲደረግ የዋለ ሲሆን በደቡብ ክልል ሶስት ከተሞችም ተቃውሞ ሲደረግ መዋሉን የተለያዩ ምንጮች ጠቁሟል::

  በደቡብ ክልል በከምባታ ዞን በዱራሜ ሺናሾና ሀድሮ ከተሞች ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ ተቃውሞ ተነስቶ የነበረ ሲሆን በነዚህ ከተሞች የንግድ አገልግሎት ቆሞ መዋሉም ተሰምቷል:: “ዳውን ዳውን ወያኔ”፤ “ወገኖቻችንን መግደል ይብቃ”፤ “አካባቢያችን በልማት ኋላ ቀርቷል”፤ “የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ” እና ሌሎችም መሰል የተቃውሞ መፈክሮችን እያሰሙ እንደዋሉ የደረሰን መረጃ አመልክቷል::
  በሌላ በኩልም በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን ውጥረት እንዳለ ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች ያስረዳሉ:: ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ መንግስት በኦሮሚያና በአማራ ክልል ባለው ውጥረት የተነሳ ዜጎቹ ወደነዚህ ክልሎች የሚያደርገው ጉዞ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ አውጥቷል::

 

 

 

 

No comments:

Post a Comment