Friday, February 16, 2018

ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው ወደ ግዛቴ ገብተዋል ያለቻቸውን 50 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የማላዊ የስደተኞች ጉዳይ አስታወቀ።



  ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ሕጋዊ የጉዞ ሰነዶችን ሳያሟሉ በሰሜናዊ የማላዊ ግዛት ሲገቡ መያዛቸውን የስደተኞች ጉዳይ ቃል አቀባይ የሆኑት ፍራንሲስ ቺቲንቡሊ ገልጸዋል።

  ስደተኞቹ እድሜያቸው በአማካኝ ከ15 እስከ 40 ዓመት የሚገመቱ ሲሆን ሚቢያ ከሚባለው የታንዛኒያ ግዛት ጀልባ ተከራይተው ወደ ማላዊ ኒካታ አውራጃ የባህር ዳርቻ ይጓዙ ነበር።

  ባሳለፍነው ሳምንትም ሞዛምቢክ 50 ኢትዮጵያውያንን ከሃገሯ ማባረሯን በዜና እወጃችን ኣሰራጭተን ነበር። በኢትዮጵያ እየከፋ በመጣው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የተነሳ በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሃገር ጥለው እንደሚሰደዱ መረጃዎች ያመለክታሉ።

No comments:

Post a Comment