Saturday, March 31, 2018

አለማቀፉ የፕሬስ ተቋም የእነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨመሮ 12 ሰዎች መልሶ መታሰር በጽኑ አወገዘ።



ተቋሙ እስክንድር ነጋን ጨምሮ እንደገና የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖሎቲከኞች በአስቸኳይእንዲለቀቁ ጥሪ አድርጓል። የእነእስክንድር ነጋ መልሶ መታሰር በኢትዮጵያ የስርአትለውጥ እንደሚያስፈልግ አመላካች መሆኑን ደግሞ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ገልጿል።
የአለም አቀፉ የፕሬስ ተቋም /አይፒአይ/ ምክትል ዳይሬክተር ስኮትግሪፊን እንዳሉት ከዚህ ቀደም እስረኞች ሲለቀቁ በኢትዮጵያ መልካም ነገር ይመጣል የሚል ተስፋ ተሰንቆ ነበር። ይህም ሆኖ ግን የእነእስክንድር ነጋ ተመልሶ መታሰር እጅግ የሚያበሳጭና ተስፋን የሚያጨልም መሆኑን ምክትል ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
እናም አስቸኳይጊዜ አዋጁ ሕግና ስርአትን ለማስከበር የወጣ ሳይሆን ዜጎችን አፍኖ ለመግዛት ያለ መመሆኑን ያሳያል ብሎዋል።
ይህበ እንዲህ እንዳለም የድርጅቱ የምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ አቶ ፍስሐ ተክሌለ አሜሪካ ድምጽ እንደገለጹት ደግሞ በኢትዮጵያ ሕግና ስርአት እንደሌለ ያስረዳሉ። እንዲሁም ሰዎችን እየፈቱ ማሰር ለውጥ እንደማያመጣምነው ጨምሮ የገለጹት።

No comments:

Post a Comment