Saturday, March 31, 2018

ወታደራዊ እዙ በመተማ ዮሃንስ ያዘጋጀው ስብሰባ በተቃውሞ መቋረጡ ታወቀ።



እንደ መረጃው ጥቆማ፣ በኣማራ ክልል መተማ ዮሃንስ ከተማበ ቀበሌ 03  አዳራሽ፣እሁድ መጋቢት  15/2010 ዓ.ም ወታደራዊ እዙ ያዘጋጀው ስብሰባ በተቃውሞ መቋረጡ  ለማወቅ ተችለዋል።
ወታደራዊ እዙ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ ከመተማ ህዝብ ጋር ስብሰባ ለማድረግ የሞከረው እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁከትና ብጥብጥ ምክንያት ስብሰባው ተቋርጧል።ህዝቡበስብሰባው ካነሳቸው ጥያቄ ጥቂቶቹ፣ ለሱዳንተቆርሶየተሰጠውየአባቶቻችንርስትበአስቸኳይይመለስልን፣ በማስፈራራትስልጣንማራዘምአይቻልም” የሚሉናሌሎችበርካታጥያቄዎችተነስተዋል።
ህዝቡ ጥያቄዎች ሲነሱ ድጋፉን በጭብጨባና በፉጨት የገለጸ ሲሆን፣ ጸጥታ ለማስከበር የተሳናቸው የመድረኩ መሪዎች የፌድራል ፖሊስና መከላከያ ሰራዊት ጠርተዋል። ህዝቡም በብስጭት “ፍርሃት ኣይወክለንም”  በማለት መድረኩን ረግጦ እንደወጣ የተገኘው መረጃ ጠቁመዋል። ስብሰባውን ከምዕራብ  እዝ ኮ/ል ተሾመ የተባለ እንዲሁምየ ከተማው የአስተዳደርና ጸጥታ ሃላፊ አቶ ለምለሙ ባዬ እንደመሩት ታውቋል።

No comments:

Post a Comment