Saturday, March 31, 2018

የኢህኣዴግ ገዢ ስርዓት ለቀናት በቆየ ስብሰባው ዶክተር ኣብይ ኣህመድ ጠቅላይ ሚንስተር መምረጡ ለተናሳው የህዝብ ጥያቄ ምላሽ እንደማይሰጥ ተገለፀ።



ለተከታታይ 8 ቀናት በዝግ አደራሽ ሲቦጫጨቅየ ቆየው የኢህአዴግ ስራ ኣስፈፃሚ፣ያለአንዳች ለውጥና አቅጣጫ ወደ የኢህአዴግ ምክርቤት በማምራት ከ8 ቀናት በሃላ ስብሰባው ለነባሩ ጠቅላይ ሚኒስተር በማውረድ ዶ/ር ኣብይ አህመድ ሞሾም ለተነሳው የህዝብጥ ያቄና ፖሎቲካዊ አለመረጋጋት መፍትሄ ሊያመጣ እንደማይችል እየተገለፀ ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል መንስኤው ከኢህኣዴግ ስርአት ዓፈናና ምዝመዛን በመላቀቅ፣ የህዝብ አገልጋይ ሆኖ የህዝብ ጥያቄና ፍላጎት ብቅፅበት ምላሽ የሚሰጥ፤ የህዝብ ጥቅም የሚያረጋግጥ፤ ህዝብ የወከለው ዴሞክራስያዊ ስርዓት ለማምጣት እንጂ የኢህአዴግ ቡድን ከውስጡ የሚያደርጋቸው የግለሰዎች መሾም ናመሻር ለውጥ የለውም በመባል የተለያዩ ወገኖች በመግለፅ ላይ ናቸው።

በመጨረሻ ፣የኢህኣዴግ ስርአት በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ እያደረጋቸው ያለ፣ የተለመዱ የሹምሽር እንቅስቃሴዎች የተጀመረው የህዝብ ትግልና እንቅስቃሴ እንዳያሰናክለውና፣ እንዲሁም በባሰ መልኩ ውድመት እንዳያስከትል ሁላችን ኢትዮጵያውያን የለውጥና ዴሞክራሲ ፈላጊዎች ትግላችን እናበረታታ በማለት በወቅታዊ ጉዳይ ትኩረት በማድረግ የሚተነትኑ ወገኖች ገልፀዋል።

 

No comments:

Post a Comment