Saturday, March 31, 2018

በትግራይ ክልል እየተካየደ ያለው የህዝብ ኮንፈረንስ ከዚህ በፊት ከተካሄደው ለውጥአል ባመድረክ እንደማይለይ እየተገለፀ ነው።



19  መጋቢት  2010 ዓ/ም  የተጀመረው ለተከታታይ 4 ቀናት ይቆያል የተባለው በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው የህዝብ ኮንፈረንስ፣ ከአሁን በፊት በህወሓት አመራርና ካድሬዎች የታካሄዱ ፍሬ ያልተገኙባቸው መድረኮች የአሁኑ ደግሞ ተቀጥያ መሆኑ ተጠቁሟል።

የህወሓት አመራር የአምባገነን አስተዳደርና ብሉሽነት በመከተሉ ምክንያት ሃገራዊና ክልላዊ ተሰሚነት በመነፈጉ በስልጣኑ ለማቆየት የሚያግዙ የተለያዩ ፈጠራዎች ሲያካሂድ መቆየቱ የሚታወስ ሆኖ፣ አሁን ደግሞ "ኮንፈረንሳችን ለሰላም፣ ለልማት ለዴሞክራሲ "በሚል መሪ ቃል በክልል ደረጃ የህዝብ ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው።

በመጨረሻ ፣ለውጥ የማያመጡ በህወሓት አመራሮች የሚካሄዱ ኮንፈረንሶች ህዝቡ መቃወም እንዳለበትና ከዛ ባለፈም ህወሓት ከማይወጣበት ኣዘቅት በገባበት ወቅት የሚሰጣቸው ተስፋዎች በተግባር በመተርጎም ለሚነሳው የህዝብ ጥያቄ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ይገባል ተባለ።

 

No comments:

Post a Comment