Saturday, March 31, 2018

በሞያሌ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ወደ ኬንያ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር መጨመሩን አለም አቀፉ ቀይ መስቀል አስታወቀ።



መንግስት ስደተኞቹ እየተመለሱ መሆናቸውን ቢገልጽም አለም አቀፉ ቀይ መስቀል ባለፈው ቀናት እንዳስታወቀው በየቀኑ 500 ሰዎች እየተሰደዱ ኬንያ በመግባት ላይ ይገኛሉ ብሎዋል።
ችግሩ በተፈጠረ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ቀናት 8 ሺ 200 ኢትዮጵያውያን መሰደዳቸውን ያስታወሰውአለም አቀፉ ቀይ መስቀል በመጪዎቹ 3 ቀናት ቁጥሩ ወደ  15ሺ እንደሚያሻቅብም አስታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን፣ የኬንያ ቀይ መስቀልና የስደተኞች ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ባደረጉት ምዝገባ በመጋቢት ወር ብቻ ከሞያሌ ግድያ ጋር በተያያዘ ድንበር አቋርጠው ኬንያየ ገቡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እስካለፈው ሳምንት 10,557 ደርሷል ብሎዋል። አንዳንድ ስደተኞች የቤት እንስሳትን ጭምር ይዘው መሰደዳቸውም ይፋ ሆኗል።
የአለምአቀፉን ቀይ መስቀል እንዳስታውቀው ባለፉት 15 ቀናት ኬንያ ከገቡት ኢትዮጵያውያን  ወስጥ 615 ነፍሰጡሮች ሲሆኑ  940ዎቹ  ደግሞ አራስ እናቶች መሆናቸው ተመልክቷል። እድሜያቸው  ከ5  አመት በታች የሆኑት ሕጻናት ቁጥር ደግሞ  1,478  መሆኑ ታውቋል። 125 ሕጻናት ደግሞ ወላጅም ሆነ አሳዳጊ ሳይኖራቸው መሰደዳቸውን ከሪፖርቱ መረዳት ተችሏል። 176 አዛውንቶችም ከተሰደዱት ውስጥ መሆናቸው ታውቋል።

No comments:

Post a Comment