በተለያዩ የሽብርተኝነት ወንጀሎች ታስረው ሲሰቃዩ የነበሩ የአርባምንጭ ከተማ ወጣቶች፣ በኢትዮጵያ የተካሄደውን
ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ የተፈቱ ቢሆንም፣ በአካባቢያቸው የሚገኙ የወታደራዊ እዙ ወኪሎች ነን የሚሉ እና የወረዳው
ባለ ስልጣናት እየዛቱባቸው መሆኑ ታውቋል።
በእነ ሉሉ መሰለ መዝገብ ተከሶ በቅርቡ ከእስር የተፈታው መርደኪዮስ ሽብሩ መልሶ እንዲታሰር የተደረገ ሲሆን፣
መልካሙ ዳዲ የተባለው ሌላው በቅርብ የተፈታው እስረኛ ደግሞ በደረሰበት ድብደባ የተነሳ ወደ ወላይታ ክርስቲያን ሪፈራል
ሆስፒታል ተወስዷል።
በሌላ በኩል ደግሞ የፌደራል ፖሊስ አባል የነበረውና በድብደባ ብዛት መኮላሸቱን ልብሱን አውልቆ ለፍርድ ቤት ያሳየው
አስቻለው ደሴ ጨለማ ቤት መታሰሩ ታውቋል። አስቻለው ፍርድ ቤት ቀርቦ አላመየሁ ታከለ በተባለ ግለሰብ ምስክር ቀርቦበታል።
No comments:
Post a Comment