Wednesday, May 2, 2018

መንግስት ለሜቴክ የተሰጠውን የማዳበሪያ ፋብሪካ በመቀማት ለአለማቀፍ ጨረታ ሊያቀርብ መሆኑ ተጠቆመ።



  የያዩ የማዳበሪያ ፋብሪካን ለመገንባት መንግስት ለሜቴክ ቢሰጥም፣ ተቋሙ ግን በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከማባከን ውጭ ይህ ነው የሚባል ስራ ሳይሰራ ቆይቷል። የመንግስት ድርጅቶች የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ እንደገለጹት፣ የኮንትራት ስምምነቱ እንደሚቋረጥና ስራው ለሌላ ኩባንያ እንደሚሰጥ ስምምነት ያለ ቢሆንም፣ የመጨረሻ ውሳኔ ግን አልተሰጠበትም። በአዲሱ ጨረታ የአለማቀፍ ኩባንያዎች ጭምር ሊሳተፉበት እንደሚችሉ ባለስልጣኑ ገልጸዋል።
  ሜቴክ የያያ የማዳበሪያ ፋብሪካን በሁለት አመት ስርቶ ለመጨረስ የዛሬ 6 አመት ከመንግስት ጋር የ 11 ቢሊዮን ብር ስምምነት ፈርሞ ነበር። ከ6 አመት በሁዋላ ደግሞ ስራው በግማሽ እንኳን ሳይጠናቀቅ ተጨማሪ 20 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው ጥያቄ አቅርቦ ነበር።
  ሜቴክን ለረጅም አመታት የመሩት ጄ/ል ክንፈ ዳኘው በዝርፊያና በአስተዳደር መበላሸት ድርጅቱ ላወደመው ከ100 እስከ 200 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሃብት ተጠያቂ ሳይሆኑ ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆነው እንደተመረጡ ስልጣናቸውን ለቀዋል።


No comments:

Post a Comment