የትግራይ ህዝብ ዴምክራሲያዊ ንቅናቄ (ት.ህ.ዴ.ን) በተለያዩ አውደ ውጊያዎች የማረካቸውን የወያኔ-ኢህአዴግ ወታደሮች ዛሬ ሓሙስ 5/11/2004 ዓ/ም ድርጅቱ ባቀረበላቸው ሦስት አማራጮች መሰረት በፍላጎታቸው ለመሄድ ወደ መረጡት ቦታ ሸኝቷቸዋል። click her video
ትህዴን ምርኮኞችን በቁጥጥር ስር ካዋለበት ቀን ጀምሮ፣ እንደተለመደው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት የምርኮኛ አያያዝ ድንጋጌ በሚፈቅደው መሰረት ሰብአዊ መብታቸው ሳይጓደል ድርጅቱ በአቅሙ የሚችለውን ሁሉ በማድረግ እሳካሁን ድረስ ሲንከባከባቸው ከቆየ ብሁዋላ ሦስት የተለያዩ አማራጮችን በማቅረብ ምርኮኞቹ የፈለጉትን በነጻነት እንዲመርጡ ዕድሉ ሰጥቷቸዋል ።
የቀረቡት አማራጮች 1) ኢዲሞክራሲውን የኢህአዴግ ስርዓትን በመቋወም መታገል የሚፈልግ 2) ወደ ቤተሰቡ መመለስ የሚፈልግ 3) ወደ ሦስተኛ ሃገር መሄድ የሚፈልግ የሚሉ ሲሆኑ ፤ በቀረቡት አማራጮች መሰረት ምርኮኞቹ ወደየመረጡት አከባቢ በምርጫቸው መሸኘታቸው የትህዴን የምርኮኛ ማእከል ሃላፊ ታጋይ ጌታነህ በዛብህ ገልጸዋል።
ዛሬ ሓሙስ 5/11/2004 ዓ/ም ወደየመረጡት አከባቢ ከተሸኙት ምርኮኞች መካከል፦
1) ሃፍቱ ተስፋይ ፣ ከምዕራብ ትግራይ ዞን ፣ ቃፍታ ሑመራ ወረዳ ፣ ዓዲ-ሕርዲ ቀጠና ፣ የ 11 ኛ ክ/ጦር ፣ 4ኛ ሻምበል ፣ 2ኛ ጋንታ ፣ 3ኛ ጓድ ኣባል የነበረ ከብሄረ ትግራይ
2) ሙላቱ ቱላ ከምስራቅ ወለጋ ዞን ፣ ጉትዋ ወረዳ ፣ ሙቲ ቀበሌ ፣ የ23ኛ ክ/ጦር ፣ 3ኛ ሬጅመንት ፣ የእግረኛ መሃንዲስ አባል የነበረ ከብሄረ ኦሮሞ
3) ጎይትኦም ወ/ጅወርጊስ ከትግራይ ምዕራባዊ ዞን ፣ ታሕታይ አድያቦ ወረዳ ፣ የዓዲ-ፀፀር ቀጠና አስተዳደር የነበረ
4) መኮነን ደስታ ከትግራይ ማእከላዊ ዞን ፣ መረብ ለኸ ወረዳ ፣ ዓዲ-ሹምብሩህ ቀጠና ፣ የዓዲ-ዕቑባላሰ ሚሊሽያና አስተዳደር የነበረ
5) መኮነን ገ/ስላሴ ከትግራይ ምዕራባዊ ዞን ፣ ዓዲ-ዳዕሮ ወረዳ ፣ ዕጉብ ቀጠና የዓዲ-ርእሶ ቀበሌ ሚሊሽያ የነበረ
6) Þ/አ መኮነን አምታታው ከሰሜን ሽዋ ዞን ፣ መሃል ሜዳ ወረዳ ፣ 02 ቀበሌ ፣ የ11ና ክ/ጦር ፣ 3ኛ ሬጅመንት ፣ 4ኛ ሻምበል ፣ 2ኛ ጋንታ ፣ 4ኛ ጓድ ኣባል የነበረ ከብሄረ አማራ
7) በርሀ ሊላይ ከትግራይ ማእከላዊ ዞን ፣ ከመረብ ለኸ ወረዳ ፣ ከዓዲ-ሽምብሩ ቀጠና ፣ ዓዲ-ዕቑባላሰ ቀበሌ ሚሊሽያ የነበረ
8) በየነ ሓጎስ ከትግርይ ማእከላዊ ዞን ፣ አሕፈሮም ወረዳ ፣ ሰምሃል ቀጠና ፣ የእንዳርጋብ ቀጠና የሚሊሽያ ሃላፊ የነበረ
9) ታደሰ ስዩም በትግራይ ሰሜን ምዕራብ ዞን ፣ በታሕታይ አድያቦ ወረዳ ፣ ዓዲ-ጸጸር ቀጠና በኮሶ ገዳይ ቀበሌ የደህንነት አባል የነበረ
10) በየነ ተስፋንክኤል በትግራይ ማእከላዊ ዞን ፣ መረብ-ለኸ ወረዳ ፣ ዓዲ-ሽምብሩህ ቀጠና ፣ ዓዲ-ዕቑባላሰ ቀበሌ ሚሊሽያ የነበረ ይገኙባቸዋል።
ከዚህ ቀደም ትህዴን በተለያዩ አውደ ውጊያዎች የማረካቸውን የጸረ-ዴሞክራሲው ስርዓት ወታደሮች በተለያዩ ግዚያት ወደየ መረጡበት አከባቢ መሸኘቱን የሚታወስ ነው።
Email;- tpdm1993@yahoo.co hadnet93@demhit.com
facebook;- ህዝባዊ ተቓላሳይ
No comments:
Post a Comment