Thursday, August 23, 2012

ድርጅታዊ መግለጫ


በአምባገነኑ የወያኔ-ኢህአደግ ስርዓት አመራር መለስ ዜናዊ ሞት ምክንያት ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ት.ህ.ዴ.ን)የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ!

በቅድሚያ ከደርግ ስርዓት ውድቀት ማግስት ጀምሮ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ለ 21 ዓመታት በአመራርነት ተቀምጦ የንፁሃን ደም እያፈሰሰ የቆየ የአምባገነኑ አመራር መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ በባህሉ በበዳዮችም ላይ ቢሆን ሞት የማይመኝ ቢሆንም ሁኔታው ሰላምንና ፍትህን ለሚሹ ሁሉ መጠነኛ እፎይታ የሚሰጥ ነው።
መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብ ከረጅም አመታት ጀምሮ ብሄራዊና መደባዊ ጭቆናን በመቃወም ያካሄድከውን ተጋድሎና አሁን እያካሄድከው ያለውን መራራ ህዝባዊ ትግል ለሃገር ነጻነትና ክብር ሲባል መሆኑን ምንም ጥርጥር የለውም።
ህዝባችን ለዘመናት ተጭኖት የነበረውን የጭቆናና ብዝበዛ ቀንበር ከላው ላይ አሽቀንጥሮ በመጣል አንዲት የበለጸገች ዴሞክራሲያዊት ሃገር እውን ሆና ማየት በነበረው ፍላጎት በሽዎች የሞቆጠሩ ጀግኖች ክቡር ህይወት ከፍሎ ወደ ሚፈለገው መድረክ ቢደርስም ፣ የወያኔ-ኢህአደግ ስርዓት ሽሞኞች የኢትዮጵያን ህዝብ ደምንና አጥንትን ተሻገርው በህዝቡ ላይ ክህደት በመፈጸም የሃገሪቱን አንድነት በማዳከም ህዝቡ እርስ በራሱ በጠላትነት ዓይን እንዲተያይ በማድረግ የተነሳለትን ሃገርን የማዳን ትግል ሙሉ በሙሉ አክሽፈውበታል።
የወያኔ-ኢህአዴግ ስርዓት በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ አመራር ሰጭነት  በህዝብ ላይ የፈጸመው በደል ፣ ለአመታት የዚሁ ስርዓት ሞልቶ የተትረፈረፈውን የግፍ ጽዋ ሰለባ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ከማንኛውም በላይ ጠንቅቆ ያውቀዋል። ይህ በመለስ ዜናዊና ተከታዮቹ ቀጥተኛ ትእዛዝ በዜጎች ላይ ሲፈጸም የቆየ በደል የስርዓቱና የሌሎዎቹን እድሜ ለማራዘም ሲባል ህገ-መንግስቱን በማን አለብኝነት በመጣስ የመብት ጥያቄዎችን በሚያነሱ ሁሉ ከግል እስከ በዘር የሚገለጽ ኢዴሞክራሲያዊ ተግባራት እየፈፀሙ እንደመጡ የአለም ማህበረሰብ የሚያውቀው ሃቅ ነው።
እንዲህ ያለውን ፈላጭ ቆራጭ አመራር በሞት ሲለይ ሃገሪቱ እንደ አንድ ህዝብና ሃገር ወዳድ አመራር እንዳጣች ተደርጎ የሚወሰድ ሳይሆን እንደ አንድ ጸረ-ህዝብ ሃገሪቱና አከባቢውን ባጠቃላይ ሲያተራምስ የነበረ አመራር መወገድና አንድ እርምጃ ወደፊት ተደርጎ መወሰድ ይገባዋል።
ነግር ግን የወያኔ-ኢህአደግ ስርዓት ቁንጮ የሆነው መለስ ዜናዊ በሞት መለየት እንደ የርስዓቱ የመጨረሻ ሞት ተደርጎ የሚወሰድ ስላልሆነ በመለስ ዜናዊ አመራር ስር ሆነው ሃገርን ያደሙና በርካታ ግፈቹን የፈጸሙ  ባምሳልም በተግባርም የማይለዩ  የስርዓቱ አገልጋዮችና ተጠቃሚዎች የሆኑ ጸረ-ህዝቦች ስላሉ በመለስ ሞት ምክንያት ጥገናዊ እንጂ መሰረታዊ ለውጥ ሊመጣ አይችልም። በመሆኑም የኢትዮጵያ ህዝብ ለጉዳዩ ከፍተኛ ግምት በመስጠት የሃገራችንን እጣ ፈንታ ከከፋ ወደ ባሰ  እንዳያመራ ሁኔታውን በጥንቃቄ ሊከታተለውና ለመሰረታዊ ልወጥ ሊነሳሳ ይገባል።
በመጨረሻም፦ በሃገራችን በተለያዩ አከባቢዎችና ከሃገር ውጭ የሚገኙ ተቋዋሚ ድርጅቶች ፣ ሲቪል ማህበራትና ግለ-ሰቦች ባጠቃላይ ሲያካሂዱት የቆይቱን ህዝባዊ ትግል ፣ ለውጥ ለማምጣት እየከፈሉት ያሉትን መስዋእትነትንና እየተፈጠረ ያለውን የተሻለ የትግል ሁኔታ በመጠቀም ከጠባብ አከባቢያዊና ብሄራዊ ስሜት ተላቀው ነጻ ሃገራዊ አስተሳሰብ ይዘው ከማንኛውም ግዜ በላይ አንድነታቸውን አጠናክረው ህዝባዊ ትግላቸውን ሊቀጡሉበት ይገባል በማለት የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ትህዴን)  በዚሁ አጋጣሚ ከሁሉም በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ ተቃዋሚ ድርጅቶች ፣ ሲቪል ማህበራትና ግለሰቦች ጋር ዛሬም እንደትላንቱ ሁሉ አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑ ይገልጻል።  
                       ዘላለማዊ ህዝብ እንጂ ዘላለማዊ ስርዓት የለም!!
                                    ድል ለጭቁኖች!!
                               ነሃሴ 17/12/2004 ዓ/ም
Email;-  tpdm1993@yahoo.co    hadnet93@demhit.com    
                      ዴ.ም.ህ.ት ቪድዮ  

No comments:

Post a Comment