Monday, July 15, 2013

በአዲስ አበባ ከተማ በፕያሳ አከባቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አንድ ሰራተኛ ከባንኩ ማናጄር ጋር በመመሳጠር 3 ሚልዮን ብር ዘርፎ መጥፋቱን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።



በደረሰን ዘገባ መሰረት በፕያሳ አከባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ተቀጥሮ በሞያው ሲያገለግል የነበረው አቶ ዮዋሃንስ ተስፋየ ሰኔ 4,2005 ዓ/ም ከባንኩ ማኔጀር ጋር በመነጋገር ለስራ ይፈለጋል በሚል ሰበብ 3 ሚልዮን ብር ይዞ እንዲወጣና አንድ ሚልዮን ብር ለባንኩ ማናጄር በመተው ቀሪውን ይዞ እንዲሰወር ተስማምተው ሲያበቁ ሰራተኛው ግን የዘረፈውን ገንዘብ በሙሉ ይዞ መጥፋቱን ቷውቋል።
ሰራተኛውና የባንክ ቤቱ ማናጀር ተስማምተው ከባንኩ ወጪ እንዲሆን የተደረገው ገንዘብ ግለሰቦቹ ያላቸውን ሃላፊነትና የስራ ክፍፍልን ተጠቅመው ህጋዊ በሚመስል መንገድ የባንኩ ማናጀር በግብሩ-አበሩ ዮዋሃንስ ተስፋየ ስም የተጠቀሰው ገንዘብ ወጪ እንዲሆን የሚገልጽ ማዘዣ ደብዳቤ በማዘጋጀትና በመፈረም የባንክ ቤቱን ገንዘብ ያዥ በማተለል ወጪ እንዲሆን የተደረገ ነው።
ማናጀሩ ገንዘቡን ለስራ ወጪ እንደሆነና ነገር ግን ሰራተኛው ዮዋሃንስ ተስፋየ ሃላፊነቱን በመዘንጋት ይዞት እንደጠፋ በማስመሰል ከተዘረፈው ገንዘብ አንድ ሚልዮን ብር በመውሰድና በጠፋው ሰራተኛ በማሳበብ እራሱን ነጻ በማውጣት በስራው ለመቀጠል በሚያስችለው መንገድ የፈጸመው መሆኑ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።