Monday, July 15, 2013

ከተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች በተለያየ ምክንያት ወደ ባህርዳር ከተማ የሚሄዱ ዜጎች አሸባሪዎች በሚል ሰበብ እየታሰሩ ነው።

በሙስናና በከፋፋይነቱ በህዝብ ዘንድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠላ የመጣው የኢህአዴግ ስርዓት የዜጎችን ከአንድ ክልል ወደ ሌላው ክልል የመሄድ ፤ የመኖርና የመንቀሳቀስ መብት በመጣስ በተለይም በወጣቱ መካከል የሚደረጉትን ግንኝነቶችን በጥርጣሬ ዓይን በማየት በባህርዳር ከተማ ለሚገኙ ከሌላ ክልል የሄዱ ወጣቶችን ከየስራ ቦታቸውና ከማረፊያ ቤታቸው በማስወጣት ምን ልትሰሩ መጣችሁ መታወቅያ ወረቀታችሁን አምጡ በማለት ሰበብ እየፈጠሩ ውጣቶችን በማዋከብና በማሰር ላይ መሆናቸውን ቷውቋል።
በኢህአዴግ ስርዓት እንደወንጀለኛ ተቆጥረው በከተማዋ የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ከታሰሩት ወጣቶች አብዛኛዎቹ የመታወቅያ ካርድ የያዙ ቢሆኑም የፌደራል ፖሊስና የከተማዋ የፖሊስ አባላት እዚሁ ከተማ እንድትንቀሳቀሱና እንድትሰሩ የፈቀደላችሁ ማነው? በማለት ወጣቶችን እስር ቤት ውስጥ በማጎር እየቀጠቀጧችው መሆኑን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።