የዓዲግራት ከተማ ኗሪ የሆኑት አቶ ሰለሙን ፤ የ 10 ሚልዮን ብር ቦንድ ገዙ በማለት ነሃሴ 6,2005
ዓ/ም ድምጺ-ወያነ ሬድዮ የዘገበውን ዜና ሃሰት መሆኑን ጠቅሰው ለቦንድ ግዥ ወጪ እንደሆነ ተደርጎ የተጠቀሰው ገንዘብ መጠን የሌለኝ
መሆኑ እየታወቀ የከተማዋ የመስተዳድር አካላት ስሜን ለፕሮፓገንዳ
ስራ መጠቀማቸው ወንጀል ነው ። በተለይም ቤተሰብ ውስጥ ሁኔታው ንትርክና አለመተማመን ፈጥራል ስሉ አማረዋል።
የከተማዋ ኗሪ ህዝብ በበኩሉ ሁኔታው በስልጣን ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ ስርዓት ሃቅን ወደ ጎን በመተው
ምን ያህል ህዝብን ለማታለልና ለማደናገር የቆመ መሆኑንና ድርጊቱ የስርዓቱ ውድቀቱ እየታቃረበ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ሲሉ ተናገሩ።