እነዚህ ከዓመታት በፊት የተጠየቁትን ለኮንደሚንዮም የሚሆን ክፍያ አስቀድመው በመክፈል አዲስ ቤትን ሲጠባበቁ
የቆዩ ዜጎች ኮንዶሚንዮሙ ተገምብቶ ከተጠናቀቀ ብሁዋላ መንግስት ለባለ መብቶቹ ከማስረከብ ይልቅ ለባንክ በማስተላለፉ ነሃሴ
8,2005 ዓ/ም የኮንደሚኒዮም ቤታቸውን እንዲረከቡ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካል በጠየቁ ጊዜ ባንክ ቤትን ጠይቁ የሚል ምላሽ
እንደተሰጣቸው ይገልጻሉ።
በሁኔታው ቅር የተሰኙ ተበዳዮቹ የተነገራቸውን ንግድ ባንክ ህላፊ ሄደው ስለ ሁኔታው ቢያነጋግሩም ስለ እናንተ
ጉዳይ የምናውቀው ነገር የለም የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ይናገራሉ።