Monday, August 19, 2013

በወልዲያ ከተማ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በመለስ ፋውንዴሽን ስም ገንዘብ ለማሰባሰብ ያካሄዱት ስብሰባ ህዝባዊ ተቃውሞ አጋጠመው።




በአማራ ክልል ወልዲያ ከተማ ነሃሴ 7, 2005 ዓ/ም በተካሄደ ስብሰባ በኢህአዴግ ካድሬዎች እንደ አንድ አጀንዳ ሆኖ የቀረበው ለመለስ ፋውንዴሽን የሚሆን ገንዘብ ኗሪው ህዝብ እንዲያዋጣ ለማግባባት ነበር ። ነገር ግን  ህዝቡ በየአመቱ 11% ኢኮኖሚያዊ እድገት እያስመዘገብን ነው በማለት በሚድያ ስታስተጋቡ እንዳልነበረ ሁሉ አሁን እንዴት ህዝቡን ገንዘብ እዲያዋጣ መጠየቅ ፈለጋችሁ ? ለምን መንግስት አይሰራውም ? ችግራችን እንዳይበቃን የተለያዩ መዋጨዎችን እየፈጠራችሁ አትበዝብዙን በማለት ተቃውማቸውን ገልጸዋል።
በስብሰባው ከተገኙ የከተማዋ ኗሪዎች መካከል ህዝቡን በመወከል ተቃውማቸውን የገለጹ ሃምሳ አለቃ ንጋቱና አቶ ያሲን ከድር የተባሉ የ70 ዓመት አዛውንት ይገኙበታል።