Monday, August 19, 2013

በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎች መንግስት በጫነባቸው ከፍተኛ ግብር ምክንያት ድርጅቶቻቸውን ሸጠው ወደ ጎረቤት ሃገር እየተሰደዱ ነው።




በደረሰን ዘገባ መሰረት በከተማዋ የሚገኙ ነጋዴዎች መንግስት ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ከፍተኛ ግብር እንዲከፍሉ አስገድዳቸዋል ። ነጋዴዎቹ የተጠየቁትን ግብር ንብረታቸውን ሸጠው ከከፈሉ ብሁዋላ ድርጅቶቻቸውን ዘግተው ወደ ጎረቤት ሃገር በመሰደድ ላይ ናችው ።
መንግስት የሚያስከፍለው ግብር በጣም ከፍተኛ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ወጥነት የሌለውና አድልዎ የሚታይበት በመሆኑ ተመሳሳይ ገቢ ላላቸው ነጋዴዎች የተለያየ መጠን ያለው ግብር ሲያስከፍል ይታያል ። አንዱን መክፈል ከሚገባው በታች ሲያስከፍሉት ሌላውን ደግሞ መክፈል ከሚገባው በላይ ከፍተኛ ግብር በመጫን ከስራ ውጭ ያደርጉታል ። እንዲህ ዓይነቱ አሰራር በከተማዋ ዓመታት ያስቆጠረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ መፍትሄ አልተገኘለትም።
በተጣለባቸው ከፍተኛ ግብር ምክንያት ሃገራቸውን ጥለው ከተሰደዱ የከተማዋ ኗሪዎች መካከል፣-
1-አቶ ተስፋይ በከተማዋ ፋርማሲ የነበረውና 200 ሽህ ብር ግብር እንዲከፍል የተወሰነበት ንብረቱን ሸጦ የተጠየቀውን ግብር በመክፈል ሃገሩን ጥሎ ወደ ሱዳን የተሰደ
2-አቶ ገ/ኪዳን በከተማዋ ሆቴል የነበረው 140 ሽህ ብር ግብር እንዲከፍል ተወስኖበት ንብረቱን ሸጦ ወደ ሱዳን የተሰደደ
3-አቶ ብርሃነ በከተማዋ ቡቲክ የነበረው 165 ብር ግብር እንዲከፍል ተወስኖበት ንብረቱን ሸጦ ወደ ሳውዲ አረብያ ለመሰደድ በአ/አበባ ከተማ በሂደት ላይ የሚገኝ
እንድህ ዓይነቱ ከፍተኛ ግብር በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ ብቻ ሳይሆን በሁሉም በሃገሪቱ የሚገኙ ነጋዴዎች ላይ ተመሳሳይ ችግር እየፈጠሩ መሆኑን ይታወቃል።