በአሁኑ ጊዜ ወታደሩ ኮንትራቱን በማደስ ለሚቀጥሉት ሰባት ዓመታት በሰራዊቱ ውስጥ ተጨማሪ አገልግሎት እንዲሰጥ
ለማድረግ በመከላከያ ሚኒስትር እየተደረገ ያለውን መሯሯጥ የተቃወሙና ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ በፌርማቸው ውላቸውን
ለማደስ ፈቃደኛ ያልሆኑ የሰራዊቱ አባላት ሊደርስባቸው ከሚችል ስቃይና እስራት ለማምለጥ ሲሉ የጦር ክፍላቸውን ክደው በመኮብለል
ላይ መሆናቸውን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
እነዚህ ክፍላቸውን በመጣል በመጥፋት ላይ ያሉት በርካታ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለትራንስፖርት የሚሆን
ገንዘብ በማጣታቸው ምክንያት በየከተማው ተበታትነው እንደሚገኙ ቷውቋል።