Saturday, August 24, 2013

መንግስት ስለ ግብር አከፋፈል አሰራርን በተመለከተ ከሑመራ ከተማ ነጋዴዎች ጋር ያካሄደው ስብሰባ ያለመግባባት ተበተነ።




የኢህአዴግ መንግስት ልኡካን ቡድን ስለ ግብር አከፋፈል አሰራር በተመለከተ በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ፤ በሑመራ ከተማ ከሚገኙ ነጋዴዎች ጋር ነሃሴ 9 እና10,2005 ዓ/ም ባደረገው ስብሰባ በተሰብሳቢዎች የቀረበ ሃሳብና ጥያቄ በአግባቡ ማስተናገድና ምላሽ መስጠት ስላልቻለ ስብሰባው ያለ ምንም ፍሬ መበተኑን ቷውቋል።
ስብሰባውን ለመምራት የተላኩ የመንግስት ባለስልጣናት ነጋዴው እየከፈለው ባለው ግብር መንግስት ደስተኛ መሆኑን በመግለጽ ስብሰባውን ለመክፈት የተያዘውን አጀንዳ ለመጀመር ሲሉ ተሰብስቢዎቹ እውነት ብላችሃል ነጋዴው መንግስት የሚጥልበትን ከፍተኛና ኢፍትሃዊ ግብር በሚያገኘው ገቢ መሸፈን አቅቶት ንብረቱን በመሸጥ እንዲከፍል ሲገደድና ለኪሳራ ሲዳረግ መንግስት ደስተኛ ሊሆን ይችላል። እኛ በአሁኑ ጊዜ የነበረንን ሃብት በግብር ስም በመንግስት በመዘረፉና የምንቀሳቀስበት ካፒታል በማጣታችን ስርተን ወደ እምኖርበት አገር እንድንሄድ ባይሆን ተባበሩን በማለት በምሬት በመናገራቸው የተነሳ የተያዘው አጀንዳ ሳይጠቃለል ስብሰባው ሊበተን ችሏል።