አምባገነኑ የኢህአዴግ ስርዓት በሚከተለው ብልሹ አሰራር ምክንያት የመንግስት ባለስልጣናት የንግዱን እንቅስቃሴንና
የነጋዴውን ወጪና ገቢን በሚገባ ሳያጤኑ ሆን ብለው የንግድ ድርጅቶችን በማዳከም ነጋዴውን ለማንበርከክ አቅደው ስለሚንቀሳቀሱ የችግሩ
ሰለባ የሆኑ ነጋዴዎች ለሚያቀርቡት አቤቱታ አስፈላጊውን ቱክረት በመስጠት በተገቢውን ማስተናገድ ሲገባ ሃላፊነታቸውን በመዘንጋት
ነጋዴውን ለማነጋገር ፈቃደኛ አይደሉም ሲሉ የከተማዋ ነጋዴዎች ያማርራሉ።
መንግስት በሚጥለው ከፍተኛ ግብር ምክንያት ችግር ላይ ከወደቁ የከተማዋ ኗሪዎች መካከል
1-አቶ ዘውደ አረፋይነ በከተማዋ ሻይ ቤት ያለው ሲሆን 17 ሽህ እንዲከፍል የተወሰነበት።
2-አቶ ዘርኢሰናይ ሰመረ በከተማዋ የሸቀጣሸቀጥ ድርጅት ያለው ሲሆን 130 ሽህ ብር ግብር እንዲከፍል የተወሰነበት።
3-አቶ ወ/ኪዳን በከተማዋ ጫማ ቤት ያለውና 36 ሽህ ብር የመንግስት ግብር እንዲከፍል የተወሰነበት።
በከተማዋ የሚገኙ በርካታ ነጋዴዎች መንግስት በሚጥልባቸው ከፍተኛ ግብር ምክንያት ድርጅቶቻቸውን ዘግተው
አገሪቱን ጥለው ወደ ውጭ በሰደዳቸውን የሚታወቅ ነው።